Get Mystery Box with random crypto!

'ፕራንከ በማድረግ የሚታወቀው ሶሀቢይ' ~ በዚህ መልኩ ርእስ ከሰጠ በኋላ የኑ0ይማን እና የሱወይቢ | ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል

"ፕራንከ በማድረግ የሚታወቀው ሶሀቢይ"
~
በዚህ መልኩ ርእስ ከሰጠ በኋላ የኑ0ይማን እና የሱወይቢጥን "ገጠመኝ" ማስረጃ አድርጎ የጠቀሰ ሰው አየሁ። የታሪኩን ጭብጥ ከፀሀፊው ልጥፍ ቀንጨብ አድርጌ ላቅርበው፦
{{ኑአይማን ሱወይቢጥን ምግብ ጠየቀው። አቡበክር ሳይመጣ አልሰጥህም አለው። በዚህን ግዜ ኑዐይማን ቆይ እሰራልሃለሁ ብሎት ወደ ሌሎች ነጋዴዎች ዘንድ በመሄድ "ባሪያ ትገዙኛላችሁ?" አላቸው። "አዎ በስንት እንግዛህ?" አሉት። "አይ ዋጋውማ ቀላል ነው ነገር ግን ባሪያው ጉድለት አለበት ጉድለቱን ሳልነግራችሁ አልሸጥላችሁም እስከነጉድለቱ ከገዛችሁኝ ነው የምሸጥላችሁ" አላቸው። "ጉድለቱ ምንድነው ?" ብለው ሲጠይቁት "ባሪያው ምላሱ ረጂም ነው ሁሌ ነጻ ሰው ነኝ ባሪያ አይደለሁም እያለ ይለፈልፋል" አላቸው። "ጉድለቱ ይህ ብቻ ከሆነ አብሽር እንገዛሃለን" አሉት። በ 10 ትናንሽ ግመሎች ተስማሙ። ግመሎችን ሰጥተውት እየነዳቸው ወደ ሱሀይቢጥ ጋር ነጋዴዎችን ይዟቸው መጣ።  "ይሄው ባሪያው ውሰዱት" አላቸው። ሱሀይቢጥም "ኧረ ባሪያ አይደለሁም ነጻ ሰው ነኝ" ብሎ ቢጮህ "ዝም በል ይህ ነውር እንዳለብህ ቀድመን አውቀናል ዝም ብለህ ና" ብለው በገመድ አስረውት ወሰዱት።

አቡበክር ሲዲቅ  ሲነገረው ስቆ ለነጋዴዎቹ ግመሎቹን መልሶላቸው ሱሀይቢጥን አስለቀቀው። ከጎዞ ሲመለሱ ለነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ኑአይማን ሱሀይቢጥ ላይ የሰራው ፕራንክ ሲነገራች እሳቸውም ሶሀቦቻቸውም ሳቁ ኑዐይማንን አልወቀሱትም።
ኑአይማን ሌሎችም በርካታ ፕራንኮች አሉት ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አይቃወሙትም ነበር ። }}
=

እንግዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ፕራንክ እየተባሉ ለሚለቀቁ ስራዎች ማስረጃ መሆኑ ነው። ሌላም ፀሐፊ ከዚህ በፊት ይህንንና ሌሎች ቂሳዎችን በተከታታይ ሲፅፍ አይቻለሁ።
ለማንኛውም በኢስላም እንዲሁ ኪታብ ውስጥ ስለተገኘ ብቻ አንድ ዘገባ ዝም ብሎ አይወስድም። ተቀባይነቱ ይፈተሻል። የዘርፉ ማለትም የሐዲሥ ሊቃውንት ደግሞ ምርቱን ከእንክርዳዱ አበጥረው እየለዩ አስቀምጠዋል። ወደ ተነሳንበት ዘገባ ስንመለስ የሐዲሥ ምሁራን ብይን ይህንን ይመስላል፦

1- አልቡሲሪይ "ይሄ ደካማ ሰነድ ነው" ብለዋል። [ሚስባሑ ዙጃጃህ: 4/115]
2- አልባኒይ ደካማ ነው ብለዋል። [ዶዒፍ ኢብኑ ማጀህ፡ 750]
3- ሹዐይብ አልአርናኡጥ ደካማ ነው ብለዋል። [ተኽሪጁ ሙሽኪሉል ኣሣር፡ 1620] [ ተኽሪጁል ሙስነድ፡ 26687]

ይልቁንም ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ
"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"
አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ እና አሕመድ የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡

#ሼር_አድርጉት
https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki