Get Mystery Box with random crypto!

ጉዞ ወደ አንድነት ሙስሊሞች ንቁ deva አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ እህት | ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል

ጉዞ ወደ አንድነት ሙስሊሞች ንቁ

deva

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ እህት ወንድሞቼ
ዛሬ አንድ ለሙስሊሙ ኡማ ይጠቅማል ብዬ ያሰብኩትን ነገር ለናንተ አካፍላቹዋለው።

እንደ ምናውቀው እኛ ሙስሊሞች በዚ ሰዓት ላይ በብሄር በዘር በጎሳ እየተከፋፈልን የተፈጠርንበትን አላማ ዘንግተናል። ለምንድነው የተፈጠርነው???


እኛ ሙስሊሞች የተፈጠርነው የአላህን ቃል ለመታዘዝ ማለትም አላህ የፈቀደልንን በማድረግ የከለከለንን ለመከልከል ነው ነገር ግን አሁን ላይ ያለንበት ሁኔታ ስናየው ወሏሂ እጅጉን ያሳዝናል አንተ ኦሮሞ ነህ አንተ አማራ ነህ ስንባባል ላኢላ ሃኢለላ ሙሀመዱን ረሱለላህ በምትለው ቃል መተሳሰራችንን ረስተነዋል እንደገና ደሞ እኛው ሙስሊሞች ውስጥ እራሱ ትልቅ ችግር አለ ሱፊ ሰለፊ አህባሽ አረ ሌላም ብዙ አሉ እየተባባልን እንከፋፈላለን ቆይ ምን ማለት ነው ወሏሂ ያሳፍራል አርቀን እናስብ እስቲ በቃ ላኢላ ሃኢለላ ሙሀመዱን ረሱለላህ ያለ ሁሉ እህቴ ነሽ ወንድሜ ነህ አለቀ የምን ሱፊ የምን አህባሽ ነው ወሏሂ ተመካክረን በማሃላችን ያለውን ችግር መፍታት አለብን መውሊድ በመጣ ቁጥር ይከበራል አይከበርም እያልን ከራሳችን እህት ወንድሞች ጋር እየተሰዳደብን እንከፋፈላለን ቆይ መች ነው ተዋደን ሁሌም አብረን የምንቆመው ረመዳን ሲመጣ ነው አብሮነት የሚታየን ሌላ ግዜ አላህ የማይጠይቀን ነው እንዴ የሚመስለን አላህ አህባቢ እንንቃ ኡስታዞቻችን እስኪናገሩን ድረስ ዝም ብለን መቀመጥ የለብንም ወጣቶች እንነሳ በአላህ ረመዳንን በአብሮነት እንቀበለው ከረመዳን ቡኋላም አንድነታችንን አጠናክረን እንጠብቅ። አላማችን ሱፊ ሰለፊ አህባሽ የሚባለውን ክፍፍል አጥፍተን ዲናችንን መጠበቅ ነው በቅርብ ቀን ይህንን #challenge እኔና ወደ አስር ከሚሆኑ እህት ወንድሞቼ ጋር አንጀምራለን ኢንሻ አላህ።

እስቲ ሁላቹም በዚ ሀሳብ ላይ አስታይታችሁን አስቀምጡልን