Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

የቴሌግራም ቻናል አርማ drhaileleul — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የቴሌግራም ቻናል አርማ drhaileleul — ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
የሰርጥ አድራሻ: @drhaileleul
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.54K
የሰርጥ መግለጫ

📞 0974013612 በመደወል አስፈላጊዉን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን ተጭናችሁ 👉
@drhaileleulmd
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-02 07:21:32
“ዶ/ር ዳዊት ላንተ የተሠጠህ ትልቁ ሥጦታ የቱ ነው ?"
በአንድ ወቅት በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጨዋታ እንግዳ ላይ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝን ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ እንዲህ ስትል ጠየቀችው ፦ “ዶ/ር ዳዊት ላንተ የተሠጠህ ትልቁ ሥጦታ የቱ ነው ?" “ዶ/ር ዳዊት፦ ሁሌም ይህን ጥያቄ ስጠየቅ በተደጋጋሚ የምመልሰው መልስ ይሄንን ነው። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሬዝዳንት ሆኜ ስሠራ አንድ ምስኪን ገበሬ ከአምቦ አካባቢ ልጃቸው በጠና ታሞ ይዘው መጥተው እንከታተልላቸው ጀመር ልጁም ከቀን ወደ ቀን ለውጥና መሻሻል ማሳየት ጀመረ፡ አባትም ቢሮዬ ድረስ መጡ። “ዶክተር እንደው እባክህ ከድፍረት እንዳታይብኝ እባክህ ብለው ተጨናነቁ” ፤ ምንድነው አባቴ? አልኳቸው እሳቸውም ወጣ ብለው ማዳበሪያ ተሸክመው መጡ ። ማዳበሪያ ውስጥም በቆሎ እሸት ነበረ ። “ይሄ ነው የደረሰው ብለው” እሱን ሲሰጡኝ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር፡ ተርፏቸው ሳይሆን ካላቸው ላይ ነበረ ለኔ ሥጦታ ብለው ያመጡልኝ።”

መልካም የሐኪሞች ቀን!

ሰኔ 25/2015 ዓ.ም
1.4K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-21 08:06:22
የጡት ካንሰር በዓለማችን ላይ ቁጥር አንድ በሴቶች ላይ የሚከሰት ካንሰር(29%)ነው:: 99% ሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን 1% የሚሆነው ደግሞ #ወንዶች ላይ ይከሰታል::

በገዳይነትቱም ከ ሳምባ ካንሰር ቀጥሎም ሁለተኛው ገዳይ ካንሰር ነው ::

ይህ ካንሰር ወደ ከባድ ደረጃ ሳይደርስ በቀላሉ መከላከል ይቻላል፤ ነገር ግን አብዛኛው የ ህብረተሰብ ክፍል በግንዛቤ ማጣት የተነሳ ችግሩ ስር ሰዶ በ ቀዶ ጥገና (Surgery) እና ኬሞቴራፒ(chemotherapy) ህክምና እንኳን መዳን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ይደረሳል::

#የጡት ካንሰር ምልክቶች

1.በጡት ላይ የሚወጣ እባጭ፡- አብዛኛውን ጊዜ የጡት ካንሰር ሕመም ምልክት የሚሆነው ሕመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር ዓይነት ሊሆን ይችላል፡፡

2. የጡት መጠንና ቅርጽ መለያየት፡-
አንዱን ጡት ከሌላኛው ጡት ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ሕክምና በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት

4. የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ

5.የሕመም ስሜት፡- አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የሕመም ስሜት ሊኖር ይችላል::ነገር ግን የጡት አካባቢ ሕመም ሁሉ የካንሰር ሕመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡

ምልክቶቹን ማወቅ ዋነኛ በሽታውን መከላከያ ዘዴ ነውና እነዚህን ምልክቶች ሲመለከቱ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ መመርመር አስተዋይነት ነው::

መልካም ቀን

ሼር ያድርጉ
2.7K views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 17:55:17
የዓይንዎ ጤነንት ለመጠበቅ

1) ዓይንዎን በንፁኅ ውሃ መታጠብ

2) ፀሐይንም ሆነ ሰው ሠራሽ የሚያበሩ ጨረሮችን በቀጥታ በዓይንዎ አላማየት
ቀጥተኛ ጨረር በቀጥታ መመልከት ዓይንዎን ለአደጋ ያጋልጣል፡፡

3) ኮምፒዩተር ተጠቃሚ የሆነ ሰዉ ከ22 እስከ 28 ኢንች ያህል ርቆ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
በጣም ቀርቦ ማየትም ሆነ እጅግ ርቆ ማየት ለዓየን ችግር ይዳርጋል፡፡

4) ዓይንዎን በየ20 ደቂቃው ለ20 ሰኮንዶች ከኮምፒዩተር አንስተው  ያሳርፉ፡፡አንዳንዴም ዓይንዎን ወደላይ ወደታች እና ወደጎን በማድረግ ያንቀሳቅሱ፡፡

5) በዓይንዎ ላይ ያልተለመዱ ለውጦችን ካስተዋሉ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ለሐኪም ያሳዩ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!

የዶክተርን ትክክለኛ የዩትዩብ ገፅ subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።



2.4K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 17:28:13 የወሊድ መከላከያ መጠቀም የሌለባቸው እነማን ናቸዉ?

የትኛዉ የወሊድ መከላከያ የተሻለ ነዉ ?

ሙሉ ማብራሪያ በዶክተር ኃይለልዑል



2.4K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 14:23:56
የጨጓራ ቁስለት

የጨጓራ ቁስለት በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ሊከሰት ይቸላል ፡ ፡ አንደኛው Helicobacter Pylori (H pylori) በሚባለው የጨጓራ ባክቴሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ዘርፍ የሆኑት Non-steroidal anti-inflammatory drugs ናቸው ፡ ፡

የ H pylori ባክቴሪያ በርካታ ሰዎች የሚገገኝባቸው ቢሆንም ባክቴሪያው የሚገኝባቸው ሁሉ የጨጓራ ችግር ላይኖርባቸው ይችላል ፤ እንደ Advil ( Ibuprofen) እና Diclofenac ያሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ያለሃኪም ትዕዛዝ ለተለያዩ ህመሞች መውሰድ ለጨጓራ ቁስለት ሊዳርግ ይችላል፡ ፡

የጨጓራ ቁስለት ያለባቸው ሠዎች

⃰ የማቅለሽለሽ፣

⃰ የሆድ መንፋት፣

⃰ የቃር ስሜት፣

⃰ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ የሚባባስ የሆድ ህመም፣

⃰ ማስታወክ እየተባባሰ ሲሄድም ደም የቀላቀለ ትውከት፣

⃰ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣

⃰ የክብደት መቀነስ እንዲሁም የድካም ስሜት ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ ፡ ፡ እነዚህ ምልክቶች በሚያጋጥሙን ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሀኪም ማማከር አስፈላጊ ነው፡ ፡

የጨጓራ ቁስለትን ለመከላከል የምግብ እና የመጠጥ ውሃን በንፅህናና በጥንቃቄ በመጠበቅ የጨጓራ ባክቴሪያን መከላከል እንዲሁም የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በሀኪም ከተፈቀደው መጠን በላይ አለመውሰድ ይመከራል ፡ ፡

ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ
799 views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 09:38:30
ንዴት የሚያስከትለውን የጤና ችግር ያውቃሉ?

ለድንገተኛ የልብ ሕመም ያጋልጣል

በቶሎ የሚበሳጩ እና የሚናደዱ ከሆነ ራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም እያጋለጡ እንደሆነ ሊያውቁ ይገባል፡፡

አሉታዊ ስሜታዊነት ሰውነትዎን ለሕመም ያጋልጣሉ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከ85% በላይ የሚሆኑ የበሽታ ዓይነቶች ከሚኖረን ስሜት ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡

ንዴት በውስጥዎ ማመቅ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትዎን በ3 ዕጥፍ ይጨምራል

በሚናደዱ ጊዜ ንዴትዎን ለማብረድና መፍትሔ ለመፈለግ ራስዎን የሚዝናና እና ንዴትዎን ሊቀንስ ሰለሚችል ነገርን ያድርጉ፡፡ ይህን የማያደርጉ ከሆነ እራስዎን ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣሉ፡፡

የሰውነትዎን በሽታ የመከላከል አቅም ይቀንሳል

ንዴት በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኙ በሽታ ተከላካይ የሆኑ ሴሎች እንዲዳከሙ እና በቀላሉ በበሽታ እንዲጠቁ መንገድ ይክፍታል፡፡

ንዴት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እና ሌሎችንም ስለሚያስከትል ቢቻል ባይናደዱ አልያም በዕለት ተዕለት የኑሮ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ እክሎችን በተረጋጋ መንፈስና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱና ጤንነትዎን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ስል አመክራለሁ፡፡

ጤና ይስጥልኝ
2.0K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 07:16:00
እባካችሁ ለወንድማችን ቶሎ እንድረስለት

ደግነት ዳንኤል ባሳ ይባላል፤ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 5ኛ ዓመት (Clinical - ll) የሕክምና ተማሪ ነው። ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት  ባጋጠመዉ የአንገት አከባቢ ህብለ ሰረሰር እጢ በሽታ (C2 –C3 intramedullary spinal cord tumor) ክፉኛ እየታመመ ይገኛል፤ ለዚህም በአስቸኳይ ሕክምናን የማያገኝ ከሆነ በሽታዉ የመተንፈሻ ጡንቻዎችን በመጉዳት ሕይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ሕክምናዉም ሀገር ዉስጥ ስለሌለ በአስቸኳይ ወደ ዉጪ ሀገር ሄዶ እንድታከም  የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ እና ኮምብርሄንሲቨ ሆስፒታል ሕክምና ቦርድ የወሰነ ሲሆን ለዚህም ብያንስ 1.5 ሚሊዬን ብር እንደሚያስፈልገዉ ተነግሮታል፡፡ ይህም ከቤተሰቡ አቅም በላይ ስለሆነ ሁላችውም የአቅማችሁን ትብብር እንድታደርጉ ይጠይቃል።

ለትብብራቹ እናመሰግናለን

CBE
1000205065478
Deginet Daniel Bassa

Dashen Bank
5049110500011
Deginet Daniel Bassa
gofundme- https://gofund.me/69abf8d1
+251949613179 ደግነት ዳንኤል

ለበለጠ መረጃ
0941047406 ሳምሶን መስቀሌ
0909896878 ዘሪሁን ዛና
0916280514 ሙሴ ደምሴ
1.5K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 22:18:09
ሀኪሙን እናሳክመዉ

እባካችሁ አስቸኳይ ነዉ ሼር አድርጉ

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዶ/ር ታዴዎስ ሻሜቦ ይባላል። ከአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ በህክምና ዶክትሬት ከተመረቀ ጥቂት ወር ይሆነዋል ።በአሁኑ ሰዓት Gullian Barre Syndrome በሚባል በሽታ ታሞ በሐዋሳ ሪፌራል ሆስፒታል ጽኑ ሕሙማን ክፍል (ICU) ይገኛል::

ለዚህም በሽታ የሚሰጥ መድሀኒት(የአንዱ ዋጋ 350,000 ብር ) እጅግ በጣም ከፍተኛ እና በእርሱ አቅም የሚቻል ስላልሆነ እባካችሁ በምንችለዉ አቅም በአስቸኳይ እንድረስለት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000218776292 እሸቱ ሻሜቦ(ወንድሙ)

ለበለጠ መረጃ

ደ/ር አበራ ኡርክያዉ :- 0949251686
ዶ/ር ናርዶር ቶማስ :- 0926567848
1.5K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:58:30
በግል ለማግኘት ወይም ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ።



@DrHaileleulMD

ቀጠሮ ለማስያዝ ከ ቀኑ 10:00 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ብቻ በዚህ ስልክ ይደዉሉ። (0974013612)
453 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:05:00
   ዒድ ሙባረክ عيد مبارك

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444’ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
509 views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ