የጨጓራ ቁስለት
የጨጓራ ቁስለት በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ሊከሰት ይቸላል ፡ ፡ አንደኛው Helicobacter Pylori (H pylori) በሚባለው የጨጓራ ባክቴሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ዘርፍ የሆኑት Non-steroidal anti-inflammatory drugs ናቸው ፡ ፡
የ H pylori ባክቴሪያ በርካታ ሰዎች የሚገገኝባቸው ቢሆንም ባክቴሪያው የሚገኝባቸው ሁሉ የጨጓራ ችግር ላይኖርባቸው ይችላል ፤ እንደ Advil ( Ibuprofen) እና Diclofenac ያሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ያለሃኪም ትዕዛዝ ለተለያዩ ህመሞች መውሰድ ለጨጓራ ቁስለት ሊዳርግ ይችላል፡ ፡
የጨጓራ ቁስለት ያለባቸው ሠዎች
⃰ የማቅለሽለሽ፣
⃰ የሆድ መንፋት፣
⃰ የቃር ስሜት፣
⃰ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ የሚባባስ የሆድ ህመም፣
⃰ ማስታወክ እየተባባሰ ሲሄድም ደም የቀላቀለ ትውከት፣
⃰ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
⃰ የክብደት መቀነስ እንዲሁም የድካም ስሜት ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ ፡ ፡ እነዚህ ምልክቶች በሚያጋጥሙን ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሀኪም ማማከር አስፈላጊ ነው፡ ፡
የጨጓራ ቁስለትን ለመከላከል የምግብ እና የመጠጥ ውሃን በንፅህናና በጥንቃቄ በመጠበቅ የጨጓራ ባክቴሪያን መከላከል እንዲሁም የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በሀኪም ከተፈቀደው መጠን በላይ አለመውሰድ ይመከራል ፡ ፡
ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!
ጤና ይስጥልኝ