Get Mystery Box with random crypto!

ዶር ዛኪር ናይክ # [ Dr zakir nike amharic ] [ ዶ/ር ዛኪር ናይክ] [ dr zakir nike ] DR zakir amharic

የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_zakir_nike — ዶር ዛኪር ናይክ # [ Dr zakir nike amharic ] [ ዶ/ር ዛኪር ናይክ] [ dr zakir nike ] DR zakir amharic
የቴሌግራም ቻናል አርማ dr_zakir_nike — ዶር ዛኪር ናይክ # [ Dr zakir nike amharic ] [ ዶ/ር ዛኪር ናይክ] [ dr zakir nike ] DR zakir amharic
የሰርጥ አድራሻ: @dr_zakir_nike
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.95K
የሰርጥ መግለጫ

ውድና የተከበራችሁ የዚህ ግሩብ አባላቶች በሙሉ አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
በዚህ ቻናል ውስጥ የሚለቀቁ ፕሮግራሞች
> ዶ/ር ዛኪር ናይክ
> ሸህ አህመድ ዲዳት
> ቁረአንና መሰል
> አስተማሪ ኡለሞቻችን
> አስተማሪ ዳዕዋዎች...ይለቀቃሉ
ኢንሻአላህ ሁላችሁም በተቻላችሁ አቅም ትምርቶችን ለመከታተል ሞክሩ አላህ ሁላችንንም ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን::
>ሸር በማድረግ ከአጅሩ ያግኙ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 13:05:53 “አላ ቢዚክሪላሂ ተጥመኢኑል ቁሉብ!!”
በቅርቡ በግምት የስምንት ሰዐት መንገድ ከአንድ ሾፌር ጋር ተጓዝኩ፡፡ ጉዞው ለኔ በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ጉዞዎች እጅግ ልዩ ሆኖብኛል፡፡ ሾፌሩ ከኔ ጋር ከተለዋወጣቸው ጥቂት ቃላት ውጭ ይሄን ሁሉ ሰዐት ስንጓዝ ዚክር ላይ ነበር፡፡ ወላሂ እጅግ በጣም ነው የገረመኝ፡፡ እሱን አይቼ እኔም ዚክር እጀምርና ብዙም ሳልቆይ እራሴን ከሆነ የሀሳብ ባህር ውስጥ ስንቦጫረቅ አገኘዋለሁ፡፡ እመለሳለሁ፡፡ ዳግም እራሴን ከሌላ ቦታ አገኘዋለሁ፡፡ ሱብሃነላህ!!! እራሴን ታዘብኩት አልላችሁም፡፡ ነገሩ ከዚያም በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ እራሴን ተጠየፍኩት፡፡ በወንድሜ በጣም ቀናሁኝ፡፡ አላህ በተውሂድና በሱና ላይ ያፅናው ብያለሁ፡፡
ግን ወንድሞችና እህቶች ስራችን ብለን ቁጭ ብለን ዚክር ላለማረጋችን አዋጣም አላዋጣም ምክኒያት ይኖረን ይሆናል፡፡ አሰልቺ ረጃጂም ጉዞዎችን ስናደርግ አሁንም አሁንም ከማዛጋት፣ አስቀያሚ ማስታወቂዎች ላይ ከማፍጠጥ፣ … ዚክር ብናረግ ምን ነበረበት? ሱብሃለህ!!! አንዴ ሱብሃለህ ሳንል ስንት መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠናል?! ስንት ረጃጅም ሰአቶችን በከንቱ አሳልፈናል? አራት መቶ አምስት መቶ ኪሎ ሜትሩ ይቅር:: የአራትና አምስት ሰዐት መንገዱም ይቅር:: ኧረ ሌላው ቀርቶ የፒያሳ መገናኛ፣ የመርካቶ አየር ጤና መንገድም ይቅር እሩቅ ነው እንበል:: በአንዲት አጭር ፌርማታ ስንትና ስንት ዚክር ማረግ ስንት አጅር ማፈስ አይቻልም? እውነት በዚክሩ የሚገኘው አጅር በገንዘብ ቢቀየር እንዲህ እንዘናጋ ነበር? አቤት የኛ ነገር!!!
እስኪ አንድ ደቂቃ በማይፈጁ ዚክሮች የሚገኘውን አጅር ያስቡ
- “ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል ዐዚም” በሐዲስ እንደተነገረው እነኚህ ለምላስ የሚቀሉ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አረሕማን ዘንድ የተወደዱ ቃላት ናቸው፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- “ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ” ከጀነት ድልብ ሀብቶች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ጁወይሪያ ከፈጅር ሶላት እስከ ረፋድ ዚክር ስታደርግ ቆይታ “እኔ ካንቺ በኋላ አራት ከሊማዎችን ሶስት ጊዜ ደጋግሜ ብያለሁ፡፡ ብትመዘን እስካሁን አንቺ ካልሺው ትበልጣለች አሏት፡፡(ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ፣ ወሚዳደ ከሊማቲሂ)
- አንዴ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድበታል፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማድረግ ይቻላል? … እነኚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ውድ የኢስላም ወንድሞችና እህቶች ኢስላም እኮ ሂወት ነው፡፡ አይደል እንዴ? ጁሙዐ ወይም ረመዳን ብቻ ተጠብቆ ሽር ጉድ የሚባልበት ድግስ አይደለም፡፡ “የኢስላም ድንጋጌዎች በዙቡኝ” ያላቸውን ሰው “ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ” ብለው አይደል ያመላከቱት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም? ጌታችን እንዲህ ይላል፡ ((… እነዚያ ያመኑት ልቦቻቸውም አላህን በማስታወስ የሚረኩ ናቸው፡፡ አዋጅ! አላህን በማስታወስ (የአማኞች) ልቦች ይረካሉ)) (አረዕድ፡ 28) ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡ ((ጌታውን የሚያስታውስና እና የማያስታውስ ምሳሌ የህያው እና የሙት ምሳሌ ነው)) ቡኻሪና ሙስሊም፡፡ አሁን እኛ ህያዋን ነን ወይስ የቁም ሙት?
የአላህ ሰዎች ሀይላቸውም፣ ምግባቸውም፣ እስትንፋሳቸውም፣… ዚክር ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያነበብኩት የኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡ ካየሁት ቆየሁና ምናልባት በትክክል ላላሰፍረው እችላለሁ፡፡ በግርድፉ ይሄን ይመስላል፡፡ “እንደ ኢብኑ ተይሚያ ዚክር የሚያበዛ አላየሁም፡፡ በአንድ ወቅት ፈጅር ከሰገደ ጀምሮ ዚክር ያረጋል፡፡ ባለበት ሁኔታ ላይ እያለ ሰዐቱ በጣም ሄደ፣ ረፈደ፡፡ በሁኔታው ተገርሜ እያየሁት ነው፡፡ እንደተገረምኩ ገብቶታል፡፡ ዘወር ብሎ እንዲህ አለኝ፡- “ይሄ ምግቤ ነው፡፡ እሱን ካላገኘሁ ብርታት አይኖረኝም”
“ጌታችን ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን፡፡”

ibnu munewer
962 viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:35:10 ነገ_
ነገ ሰኞ ሙሐረም 10 — ዐሹራእ እንዳያልፈን ላስታውሳቹህ ብየ ነው
890 viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 23:12:06 አስቸኳይ መልዕክት አደራ አደራ

የአሹራ ፆም የፊታችን ሰኞ ይፆማል:: ከቀኑ በፊት እሁድን አልያ ማክሰኞን አስከትሎ መፆሙ ይወደዳል!
አላህ ይወፍቀን!
1.1K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 22:16:13
የአሹራ ፆም
ሙሐረም 10 ነብዩላህ ሙሳ(ዓ.ሰ) ከአንባገነኑ የፊርዓውን ጭቆና ነፃ የወጡበት ቀን ነው::
ይህን ቀን አንድ ቀን ቀደም ተብሎ ሙሐረም 9 አልያ ሙሐረም 11ን በማስከተል መፆም
ይወደዳል::
የፊታችን እሁድ የሙሀረም ወር ዘጠነኛው ቀን ነው - ረሱል ስለ አሹራ ፆም ሲናገሩ "ምናልባት
ለሚቀጥለው አመት በህይወት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም እፆማለሁ ብለዋል (ሶሒሁ ሙስሊም
1134)
ሙሐረም 10 የአሹራ ቀን ዕለተ ሰኞ ነው:: ይህን ቀን መፆም የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ)
"የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል (ሶሒሁ
ሙስሊም 1163)
ቤተሰባችንንም ሌላውንም ይህን መልዕክት እናስታውስ!
1.2K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:03:39 የምትዋሸው እናቴ ናፍቃኛለች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አንድ የስምንት አመት ልጅ እናቱን በሞት ያጣል በዚህም የተነሳ ተጫዋች
እና ደስተኛ የነበረው ልጅ ድብርታም፣ ብቻውን የሚያዝን እና ዝምተኛ ሆነ፡፡

እናቱ ከሞተች ከአመት በኃላ አባቱ ሌላ፣ ሚስት አገባ ኑሮም ቀጠለ አንድ ቀን ልጁን አባቱ ጠራውና
"በእናትህ እና በእንጀራ እናትህ መሀል ልዩነት አለ " ብሎ ጠየቀው።
ልጁም "አዎ አለ" ብሎ መለሰ፡፡
አባቱም "ልዩነታቸው ምንድን ነው?" ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡

ልጁም "እናቴ ውሸታም ነች የእንጀራ እናቴ
ግን ውሸታም አይደለችም" አለ ያልጠበቀውን መልስ ያገኘው አባትም በመገረም "ምን ማለትህ ነው?" ይለዋል ልጁም እንዲህ አለ
:
"እናቴ እያለች ጓደኞቼ ቤት እየሄድኩ እጫወት ነበር፡፡ እናቴም በተደጋጋሚ ጓደኞቼ ቤት ሄጄ መጫወቱን እንድተው ካልተውኩ ግን ምግብ እንደማትሰጠኝ ትነግረኝ ነበረ፤ ሆኖም ግን እኔን ቤት ውስጥ ስታጣኝ የምትሰራውን ስራ አቁማ እኔን ፍለጋ ትመጣ ነበር ወደ ቤትም ወስዳ ምግብ ትሰጠኝ ነበር፤ የእንጀራ እናቴ ግን ቃልዋን ታከብራለች፡፡ ለዛም ነው ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ ያልበላሁት እርቦኛል፣ እናቴም ናፍቃኛለች፡፡ "እያለ ማልቀስ ጀመረ...።
*
#እናት
እ…እዝነት ነው እቅፏ
ና…ናፍቆት ነው መራቋ
ት…ትምህርት ነው ምክሯ

ረጅም እድሜ ለእናቶቻችን
||

https://t.me/dr_zakir_nike
https://t.me/dr_zakir_nike
1.9K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 08:57:07 ወሳኝ መልዕክት ነው ሸር እናድርግ


ዚክር፣ የዘነጋነው ሃብት
~~
መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እን ደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።
አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
* "ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
* ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
* ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
* ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
* ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።
* "አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~
① ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
* ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
* ወሪዷ ነፍሲሂ፣
* ወዚነተ ዐርሺሂ፣
* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ብዙ መፈፀም ትችላለህ። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
2.4K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, edited  05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:45:29
እንኳን ደስ አላችሁ!
አልሃምዱሊላህ

የኢትዮጵያ ፌዴራል መጅሊስ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት
ሼክ ሃጂ ኢብራሂም በመሆን ተመርጠዋል

ሸይኽ ሀጂ በቀጣይ በኢትዮጵያ መጅሊስ ታሪክ ድንቅ ለውጦችን እንደሚያሳዩን ባለ ሙሉ ተስፋ ነን!!
ኢንሸ አላህ

https://t.me/dr_zakir_nike
1.2K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, edited  12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:54:43
አጭር መልዕክት
“ማንኛውም ሰው ያለ ምክንያት 1 ሰላት
አንድ ብቻ ከተወ ከገዳይ በላይ ነህ: ከአሸባሪ በላይ ነህ በአላህ ዘንድ ★ «በጭራሽ ሊያልፈን አይገባም

ሸር እናድርገው እኛ ሰምተን ዝም አንበል!
Share›› Share›› join
«t.me/Muslim_tiktok»
«t.me/Muslim_tiktok»
1.6K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:42:38 አስቸኳይ መልዕክት አደራ አደራ

ያጀመዓ ነገ እንዴት መፆም ያቅተናል

ነገ 9ኛውን የዙል ሂጃ ቀን
(አረፋ ላይ የሚቆምበትን ቀን) መፆም ያለፈውን አመትና..የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል አደራ እንፁም



ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች ሼር ያድርጉላቸው ለአንድ መልካም ነገር መሰራት ምክንያት የሆነ፣ ያ ድርጊት እንዲፈጸም ያበረታታና ያነሳሳ፣ ድርጊቱን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር ድርሻ አለው

ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪውን ያክል ምንዳ ያገኛል ብለዋል ረሱል (ﷺ)

https://t.me/+dbvB3nFw70swYTE0
999 viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, edited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 15:01:09 ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች

ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች
ይህን ወቅታዊ ማስታወሻዬን ጥቂት ጊዜያችሁን ሰውታቹ እንድታነቡት አደራ አደራ እላለሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ አና በጣም አዛኝ በሆነው
ያለንበት ወቅት በ ዱንያ ካሉት ቀናቶች በጣም በላጭ የሆኑ እና አላህ ዘንድ በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች ከሌሎች በተለየ ና በበለጠ ተወዳጅ የሚሆንበት 10ቱ ቀናት ላይ ነው ያለው

ማስታወሻዬም የሚያተኩረው በእነዚህ ውስጥ በሚገኘው በጣም ታላቅ ና ትሩፋቱ የበዛ ስለሆነው ስለ ዓረፋ
(የዙልሂጃ 9ኛው ቀን) ነው
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የዚህን ቀን ትሩፋቶች በሚገባ አብራርተዋል

ነብያችን እንዲህ ይላሉ : አላህ ሱ.ወ ከዐረፋ ቀን የበለጠ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት የሆነ አንድም ቀን የለም
ከዛም በመቀጠል ያሉት :እኔም ከኔም በፊት ከነበሩት ነብያት ካሉት ንግግር በላጩ
لا ﺇﻟﻪَ ﺇﻻَّ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻭﺣْﺪﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳﻚَ ﻟﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟﻤُﻠْﻚُ، ﻭﻟَﻪُ ﺍﻟﺤﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ
ﺷَﻲﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለው ነው::
ይህን ዚክር በብዛት በማለት እንበርታ
ሌላው ነብያችን እንዲህ ብለዋል
በላጬ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ ነው

በዚህ በላጭ በሆነው የዓረፋ(ዙልሂጃ 9) ቀን አላህ ሱ.ወ
-ከእሳት ነፃ ከሚያደርጋቸው
-ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ መሆን የፈለገ ሰው
የዓረፋን ቀን ይፁም
ነብያችን እንዲህ ይላሉ :
{የዐረፋ ቀን በመፆም አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል እንደ ሚምር እተሳሰባለሁ}
{የዐረፋ ቀን የፆመ የሆነ ሰው ተከታታይ የሆኑ የሁለት አመት ወንጀሎቹን ይማርለታል}
የተውሂድ ቃል ዚክር ማለትን ያብዛ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር
አላህ እንዲምረው እና ከእሳት ነፃ ከሚሆነው እንዲያደርገው መለመንን ያብዛ
አሏሁመ አእቲቅ ሪቃበና ሚነን ናር የምትለዋን ዱዓ በማለት አላህን እንለምን
በዚህ ቀን ዱኣ ተቀባይ መሆኑ በጣም የሚከጀልበት ነው
ለዚህም ቀን ኸይር ፈላጊ የሆነ
ሙስሊም ራሱን ባለቤቱን እህት ወንድሞቹንና ልጆቹን ይህንን የተከበረ ቀን እንዲፆሙ ይቀሰቅሳል
አላህ ሱ.ወ የዚህን ቀን ትሩፋቶች ከሚያገኙ እና ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች እንዲያደርገን እለምነዋለሁ በመልካም ዱዓቹ አትርሱኝ

ይህን አንገብጋቢ ማስታወሻ ለምታውቁትም ለማታውቁትም ሙስሊም ለሆነ አካል እንድታሰራጬ እና የመልካም ስራ ተቋዳሽ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
طلحة أحمد
1.1K viewsՏeɿԺ ԹԺԺɿՏ, 12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ