Get Mystery Box with random crypto!

አስደናቂ ነው።ለማመን ይከብዳል።#ብራቮ በአንድ አመት ውስጥ በ4 ማስተርስ ዲግሪ የተመረቀው ኢትዮጵ | Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

አስደናቂ ነው።ለማመን ይከብዳል።#ብራቮ
በአንድ አመት ውስጥ በ4 ማስተርስ ዲግሪ የተመረቀው ኢትዮጵያዊ

1. MA in International Cooperation and Humanitarian Aid (Spain)

2. MA in Executive Community Leadership from Addis Ababa University/Jönköping University (Sweden)

3. MA in International Relations and Diplomacy from Hawassa University

4. MA in Socio-Economic Development and Planning from Wolaita Sodo University

ማነው እሱ?
ኢንጂነር ደሳለኝ ዳካ ግደቦ ይባላል፣ የተወለደው በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ህሌና ቆርኬ ቀበሌ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪ በ1998 ዓ.ም ከአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ ሜዳልያ በመሸለም ነው የተመረቀው፣ እንደተመረቀ ለአጭር ጊዜ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ሰርቷል፣ የመንግስት ኃላፊነትን በገዛ ፈቃዱ በመልቀቅ የረዥም ጊዜ ህልሙ የነበረውን ከአንድ አስርት አመታት በላይ ጀምሮ በግል ጥረቱ ለማህበረሰቡ የተለያዩ በጎ ተግባር ሥራ ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

የትምህርት ጥማቱን ለማርካትና ተጨማሪ እውቀት ለመሸመት ከመጀመሪያው ድግሪ ትምህርት ዘርፍ ጋር በምንም የማይገናኝ ለቀጣይ ጉዞ ያግዛል ብሎ ያሰበውን ፈተና ተፈተነ በሚገርም ሁኔታ ከተፈተኑ ዘርፉ ተማሪዎች በበለጠ በሁሉም ከፍተኛ ማለፊያ ውጤት በማስመዝገብ ቀጠለ።

በትናንትናው ዕለት በሁለት ማስተርስ ድግሪ የማዕረግ ተመራቂ ቢሆንም ሁለቱን መድረስ ጊዜ ባለመኖሩ በሐዋሳ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ በMA in International Relations and Diplomacy (3.87) ምረቃ ቦታ ሳይገኝ በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ በአካል በመገኘት MA in Socio-Economic Development and Planning (3.97) የሜዳልያ ሽልማት በመውሰድ ተመርቋል።

በተለይም በአውሮፓ የስፔን MA in International Cooperation and Humanitarian Aid (Spain) ትምህርት በOnile እና ጥናታዊ ጽሁፍ ደግሞ በአካል የሚቀርብ ቢሆንም ካለው የስራ ጫና እንዲሁም በሀገር ውስጥ እየተማረ የነበረውን ትምህርት እንዳይስተጓጎል ጉዞ በመሰረዝ ከኢትዮጵያ ሆኖ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በዩንቨርሲቲው ተቀባይነት አግኝቶ ጥናታዊ ፅሁፍ በማቅረብ ውጤቱም ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

በሌላ በኩል አራተኛው የማስተርስ ድግሪ በExecutive Community Leadership from Addis Ababa University/Jönköping University (Sweden) ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቦዋል።

የሼፕ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ባለቤት ኢንጂነር ደሳለኝ ዳካ በዎላይታ ሻንቶ ከተማ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በራሱ ጥረት ከተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመፃፃፍ ያስገነባው የማህበረሰብ ቤተ-መጻሕፍት ህንፃ በጥቂቱ ለአብነት የሚጠቀስ ሲሆን ላይብረሪው ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ለምርምር እና ጥናት አገልግሎት የሚውሉ ከ22,000 በላይ ውድ በዘመናዊ ኮምፒተሮች ጭምር የተጫኑ መጽሐፍትን ከተለያዩ አለማት በማስመጣት ለበርካቶች በነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

#ብራቮ እንበለው

መረጃው የወላይታ ታይምስ ነው ለፋስት መረጃ ያደረሰው ቴዲ ዋና ነው!!

ሼር_ይደረግ

የፌስቡክ ገፄን ፎሎ ለማድረግ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL