Get Mystery Box with random crypto!

ከእንስሳት የሚኙ አካል ገንቢ ንጥረ-ምግቦች የተፈጨ ደም • የተፈጨ ደም መኖ የሚዘጋጀው ደም | ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia

ከእንስሳት የሚኙ አካል ገንቢ ንጥረ-ምግቦች
የተፈጨ ደም
• የተፈጨ ደም መኖ የሚዘጋጀው ደም ከደረቀ በኋላ በመፍጨት ነው፡፡ ተረፈ ምርቱ እስከ 8ዐ% የገንቢ ንጥረ መኖ
ይዘት አለው፡፡ በዶሮ መኖ ቀመር ውስጥ ከ2–4% ያልበለጠ ቢቀላቀል ጥሩ ውጤት ሊኝ ይችላል፡፡
የተፈጨ ሥጋ
• የተፈጨ ሥጋ መኖ የሚዘጋጀው የእንስሳት ሥጋ ተረፈ ምርት አድርቆ በመፍጨት ነው፡፡ ይህ መኖ ሲዘጋጅ የእንሰሳው
ፀጉር፣ሸኮና፣ቀንድ፣ፍግ፣ፈረስና የመሳሰሉት መቀላቀል የለባቸውም፡፡ የተፈጨ ሥጋ ከፍተኛ /55%/ የአካል ገኒቢ ንጥረ
ምግብ ይዘት አለው በካልሲየም እና ፎስፈረስ የበለፀገ ነው፡፡ እርጥበት አዘል የአየር ፀባይና ሙቀት ባለበት ቦታ ተረፈ
ምርተ ቆሎ የመበላሸት ባህርይ ስላለው በደረቅና ቀዝቃዛ ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡
የተፈጨ ሥጋና አጥንት
• ከተፈጨ ሥጋ ጋር ተመሣሣይ ሲሆን የሚለየው ከፍተኛ የሆነ የአጥንት ይዘት ስላለው ነው፡፡ ስለሆነም ተረፈ ምርቱ
በፎስፈረስ እና በካልሲየም ይዘቱ በጣም የበለፀገ ነው፡፡ የፎስፈረስ ይዘቱ ከ4% በላይ ሲሆን፣5ዐ% የሚሆን የገንቢ
ንጥረ መኖ ይዘት አለው፡፡
የተፈጨ አጥንት
• ከተፈጨ አጥንት መኖ የሚዘጋጀው መጀመሪያ አጥንቱን በትንት ሃይል በመቀቀል ከበቂ በላይ የሆነውን ስብና ሥጋ
ማስወገድና የተቀቀለውንና ተሰባሪ የሆነውን አጥንት በመፍጨት ነው፡፡ ይህ ተረፈ ምርት የካልሲየምና ፎስፈረስ
ምንጭ በመሆን ያገለግላላ፡፡ የአጥንት መኖ ከ30–35% ካልሲየምና 15% የፎትፈረስ ይዘት አለው፡፡

የተፈጨ አሳ (የአሳ ተረፈ-ምርት)
• የተፈጨ አሳ ከሙሉ አሳ ወይም ከተረፈ ምርት/ኦፋል/ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ የተፈጨ አሳ ከ0–4 ሣምንት እድሜ
ላላቸው የሥጋ ዶሮዎች እስከ 1ዐ% በድብልቁ ውስጥ የሚቀላቀል ሲሆን፣ለእንቁላላ ጣይ ዶሮዎች ደግሞ ከ3–5%
መቀላቀል ይችላል፡፡ ተረፈ ምርቱ ጥሩ የማዕድን ይዘት ሊኖረው፣ለዶሮዎቹ የተሻለ የተበይነት ባህርይም አለው፡፡
የተፈጨ የአሳ ተረፈ ምርት በገንቢ ንጥረ መኖ ይዘቱ በጣም የበለፀገ ስለሆነ ለዶሮዎቹ እድገት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡
ይህ ምርት በጣና ሐይቅ አካባቢ በከፍተኛ ስለሚመረት በአግባቡ መጠቀም ይቻላላ፡፡ አዘገጃጀቱን በተመለከተ የራሱ