Get Mystery Box with random crypto!

የስንዴ ፉርሽካ • ይህ የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካዎች ስንዴን ለዱቄት ሲባል በሚፈጩበት ጊዜ በተረፈ | ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia

የስንዴ ፉርሽካ
• ይህ የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካዎች ስንዴን ለዱቄት ሲባል በሚፈጩበት ጊዜ በተረፈ ምርትነት የሚወጣ ሲሆን ሸካራ
የሆነውን የውጭውን ስንዴ ሽፋን የያዘ ነው፡፡ ፉርሽካ የሃይል ሰጪ ንጥረ-ምግብ ይዘቱ አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም
የቃጫ ይዘቱ ከፍተኛ ስለሆነ በመኖው ውስጥ የሚጨመረው መጠን አነስተኛ ነው፡፡

የስንዴ ፉርሽኬሎ
ይህም የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካዎች ስንዴን ለዱቄት ሲባል በሚፈጩበት ጊዜ በተረፈ ምርትነት የሚወጣ ሌላው
ተረፈ-ምርት ነው፡፡ ፉርሽኬሎ ከፉርሽካ ቀጥሎ የሚመጣ ሲሆን በውስጡም ደቃቅ ፉርሽካ እና አነስተኛ የዱቄት
መጠን የያዘ ነው፡፡ ፉርሽካ የሃይል ሰጪ ንጥረ-ምግብ ይዘቱ ከፉርሽካ የተሻለ ነው፡፡ በተጨማሪም የቃጫ ይዘቱ
ከፉረሽካ የተሻለ ስለሆነ በመኖው ውስጥ የሚጨመረው መጠን ትንሽ ከፍ ያለ ነው፡፡
የስንዴ ሚድሊንግ
ይህ በይዘቱ ከፉርሽካ እና ከፍሩሽኬሎ መካከል የሚኝ ተረፈ ምርት በመሆኑ በማንኛውም ንጥረ ምግብ ይዘቱ በሁለቱ
ውጤቶች መካከል ይገኛል፡፡ የቃጫ ይዘቱ ከፍሩሽካ ያነሰ በመሆኑ ለዶሮዎች መኖነት ከፍሩሽካ በበለጠ መጠን
ሊደባለቅ ይችላል፡፡