Get Mystery Box with random crypto!

⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnesuba — ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnesuba — ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️
የሰርጥ አድራሻ: @dnesuba
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

ጤና ይስጥልኝ የቻናሉ ቤተሰቦች
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ ሀሳቦችን እናም መዝሙሮች ያገኙበታል
ሰለዚህ ውድ ወንድም እና እህቶቼ ይሄንን .......
በቻናላናችን የሚሰጡ ነገሮች
መንፈሳዊ ትምህርቶች
መንፈሳዊ ምክሮች
መንፈሳዊ መዝሙር
መንፈሳዊ ጥያቄዎች
መንፈሳዊ ስዕልዎች
በየለቱ ስንክሳር
አስተያየት
ሀሳብ እና ጥያቄ
https://t.me/ uME9_xX453hk

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-21 06:16:41 #መዝሙሩን ለመመልከት ይህንን ይጫኑት





መልካም ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
218 views law of Dentistry℅, edited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:02:54 .══ ✞ ❝ የንስሐ ፍሬ❞ ✞ ══
══════ ❁✿❁ ══════
ንስሐ ማለት አልቅሶ ድንግል ማርያምን አብቅሎ ክርስቶስን አፍርቶ መመገብ ነው። ንስሐ ይሉኋል እንደ አባታችን አዳም ነው፥ አዳም ገነት ያጣትን ዕፀ ሕይወት በምድር በእንባው አብቅሏታልና። ይህችውም ድንግል ማርያም ናት። ፍሬውም ለዓለሙ ሁሉ በቃ! ይኸውም ፍሬ ሕይወት ክርስቶስ ነው።
(ጸያሔ ፍኖት ከተሰኘው የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ መጽሐፍ የተቀነጨበ /ገጽ• 370)

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን

#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
80 views *The low of Dentistry℅, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:26:29
የናፍቆት ጉልበት

ከጌታው ጋር በፍፁም መዋሐድ የሚሻ የኃጢአትን ስር ነቅሎ ሊጥል ይገባዋል። ኃጢአት ወደ እግዚአብሔር መለኮታዊ ንፅህና እንዳንቀርብ ታደርጋለችና። ቅዱስ ጴጥሮስም "ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ ተለይ።"ሉቃ5:8 ያለውም ስለዚሁ ነው። ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አይደለም ወደ ጌታ መለኮታዊ ንፅሕና የምታቀርበን ከኃጢአት ጋር እየተጋደልን ልናገኛት የምትገባዋ ንፅሐ ልቡና ናት። ጌታን የሚማርክ እውነተኛ ውብ መልክ ሁላችንም ውስጥ አለች። ጌታ በመስቀል የተጠማት ይህቺ እርሷ ናት። ያያት ያድርባትም የናፈቃት ቅዱስ ቅናትም የቀናላት ይህቺ ናት። እርሱም የእርሱን መሻት ከሰማይ ወርዶ አሳይቷል። ለእርሷ ሲል ሰው ሆኗልና ሊያድርባት የማይናፍቃት ነፍስ የለችም። የእርሱ ፈቃድ/ናፍቆት ለሁሉ የተሰጠች ናት። ወደ እርሱ ፈቃድ መቅረብ ግን የሰው ልጅ ነፃ ፈቃድ ነው። በእነዚህ ሁለት ናፍቆቶች(እግዚአብሔር ከእኛ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ለመሆን የምንናፍቀው) መኃል ያለች ግንብ ደግሞ ኃጢአት ናት። በውስጣችንም ያለች የናፍቆት ጉልበት ከኃጢአት የምትለየን ናት። የኃጢአት ብዛትም ይህቺን የናፍቆት ጉልበት ታዝላለች። ማለት የልቡናን መባረድ ታመጣለች። የልቡና መባረድም ደግሞ ከጌታ ፍቅር የኃጢአት ፍቅር እንዲያይል ታደርጋለች። የኃጢአት ፍቅርም የእግዚአብሔርን ህልውና እስከመካድ ታደርሳለች። የኃጢአት ፍቅርም ከጌታ መለኮታዊ ንፅህና አላደርስ ይላትና እርሱን ከማየት ትታወራለች። ቅርቧ ቢሆንም ኃጢአት ጋርጇታልና አታየውም።

መልካም ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን
#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)

የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join
https://t.me/DNEsuba/1924
127 views *The low of Dentistry℅, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:58:04 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

ሰኔ ፴ (30) ቀን።

እንኳን ለነቢዩ ለሰማዕቱ ለካህኑ ለሐዋርያው ለመጥምቀ መለኮት ለተወለደበት (ለልደት) በዓልና በሕንደኬ ካሉ ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ ለአባ ጌራን ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ማርያና፣ ከማርታ፣ ከመነኰስ ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

+ + +
የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሰምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ። እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ። ወተፈሥሁ ፍሥሃ ፈድፋደ። ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካርያስ። ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።

+ + +
ነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው።

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት።

አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"።

ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

+ + +
ገድለኛው የሆነ አባ ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።

ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት።

በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ።

ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።

ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።

ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።

የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30ስንክሳር።


+ + +
"ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።


+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”

2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ዕለት

#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
190 views *The low of Dentistry℅, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:15:19 “የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ዕለት

#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
112 viewsfre የበዓታ, edited  19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:12:30
ተመዘን
""""""""

በሚያሳዝን ፊቱ ወደ እኔ አፍጦ ፣
አንድ ምስኪን መዛኝ መንገድ ዳር ተቀምጦ ፣
ይለኛል ተመዘን ፣
በስንቱ ልመዘን ፣
ሚዛን በበዛበት በዚች በጉድ ሀገር ፣
መመዘኑ ሳይሆን
ኪሎን ማወቁ ነው የሚያስፈራው ነገር ።

ወፈርኩኝ ቀነስኩኝ እያሉ መጨነቅ ፣
ለማይሞላ ኑሮ ሙሉ ቀን መሳቀቅ ፣
ሁሉን በመሰለው በገባው ለሚዳኝ ፣
ፍትህ እና ሚዛን አይደሉም ተጓዳኝ ፣
ሰው ራሱን ቢዳኝ ሰውን መንቀፍ ትቶ
መች ይባክን ነበር የእውነት ፍርድ አጥቶ ።

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ዕለት

#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
127 views *The low of Dentistry℅, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:22:28 ክረምት

ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም

በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

በካቴድራል፣ ቅ/ማርያምና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ የ2014ዓ.ም. መዝጊያ መርሐግብር ላይ የተሰጠ ትምህርት

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም

#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
131 views *The low of Dentistry℅, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:42:46
#ከመጽሐፈ_ምሥጢር_ውብ_ገጾች

+ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ +

“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20

"ከእኛ ወገን ክርስቲያን እየተባሉ በገዛ መንገዳቸው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ... የእንስሳ ሥጋ ከመብላት የሚከለከሉ የሰውን ሥጋ ለመብላት ግን የሚተጉ እነዚህ ናቸው"

"ስምዖን ጴጥሮስ ከሐዋርያት ሁሉ አብልጦ ክርስቶስን ወደደው:: ክርስቶስ ግን ከሐዋርያት ሁሉ አልቆ ወንጌላዊው ዮሐንስን ይወድደው ነበር::
ስለወደደው ግን አለቃ መሆንን ለዮሐንስ አልሠጠም:: እርሱ ከወደደው በላይ እርሱን የሚወደውን አለቃ አደረገው እንጂ"

"ክርስቶስን መውደድ ከወንድሞቹ ይልቅ በጴጥሮስ ላይ በዛ:: ከወንድሞቹ ይልቅ ወደ ጌታ ኢየሱስ ለመድረስ ቸኩሏልና ከመርከቢቱ ዘልሎ ወደ ባሕር ተወረወረ እንጂ በመርከብ ለመጎተት አልቆየም::
ወደ ወደደው ለመድረስ ቀደማቸው::...
የቀረው #መጽሐፈ_ምሥጥር ያገኙታል
#ከላይ_ያሉት_ለማዘዝ @haile7646
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር
157 views *The low of Dentistry℅, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:09:54 https://www.tiktok.com/@leulemekuanent/video/7084220977726377221?_r=1&u_code=0&preview_pb=0&language=en&_d=dl41bk6j7k6j2b&share_item_id=7084220977726377221&source=h5_m×tamp=1655440425&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7105766007722280710&share_link_id=09c5b875-2d9b-4847-8c05-f7905074484b&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
180 views *The low of Dentistry℅, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:57:32 ፈጣሪን አስቀድም!

ብዙ ዜሮዎች ቢኖሩና ከፊታቸው ምንም ቁጥር ባይኖር ባዶ ናቸው፤ ከዜሮዎቹ በፊት ግን አንድ ቁጥር ቢቀመጥ ግዙፍ ቁጥር ይሆናሉ።

የዚህ አለም ደስታ፣ ሀብት፣ ስኬት፣ የሰው አክብሮትና ተወዳጅነት ኖሮህ ፈጣሪን ከፊትህ ካላስቀደምክ ሁሌም ባዶነት ይሰማሀል፤ ህይወትህ ላይ ፈጣሪ ሲቀድም ግን ሁሉም ባዶነትህ በሙላት ይተካል፤ ሁሉም ሽንፈትህ በአሸናፊነት ይደመደማል። ፈጣሪን አስቀድሙ


መልካም ዕለተ ማግሰኞ

#ዲ ን እሱባለው

¶¶¶ ልዩ ልዩ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች ፣መዝሙሮችን ፣ ግጥሞችን የሚፈልጉትን የመፅሐፍ ቅዱስን ቃል

ያገኛሉ • • • • ለመቀላቀል ለሌላም ሰው ለማጋራት

╔═══❖••❖═══╗

@DNEsuba @DNEsuba
@DNEsuba @DNEsuba
@DNEsuba @DNEsuba

╚═══❖••❖═══ ╝
202 viewsfre የበዓታ, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ