Get Mystery Box with random crypto!

⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnesuba — ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnesuba — ⛪️🇪🇹@የራማው ልዑል🇪🇹 ⛪️
የሰርጥ አድራሻ: @dnesuba
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

ጤና ይስጥልኝ የቻናሉ ቤተሰቦች
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ ሀሳቦችን እናም መዝሙሮች ያገኙበታል
ሰለዚህ ውድ ወንድም እና እህቶቼ ይሄንን .......
በቻናላናችን የሚሰጡ ነገሮች
መንፈሳዊ ትምህርቶች
መንፈሳዊ ምክሮች
መንፈሳዊ መዝሙር
መንፈሳዊ ጥያቄዎች
መንፈሳዊ ስዕልዎች
በየለቱ ስንክሳር
አስተያየት
ሀሳብ እና ጥያቄ
https://t.me/ uME9_xX453hk

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 08:02:53
#ወዳጄ !!!

ልብህን የሚሰብረው ከሰዎች ብዙ መጠበቅ ነው፤ ስለዚህ ከሰዎች ብዙ አጠብቅ። እህቴ የሚከፋሽ ሌሎች የሚያደርጉልሽን ጠብቀሽ ስላላገኘሽ ነው። ከሰው መጠበቁን አቁመን ደስታችንን ከፈጣሪና ከራሳችን ልብ ውስጥ ማግኘት ነው ያለብን፤ ያኔ አንዱን ቀን ደስ ብሎን ሌላኛውን ቀን አይከፋንም ምክንያቱም ደስታችን ሌሎች ላይ ጥገኛ አይደለም።


“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ዕለት

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
162 views law of Dentistry℅, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:48:05
" ገብርኤል ሆይ ከሰው ወገን ከቶ ጠዋትና ማታ እንደ እኔ ኅዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም ከመላእክት ወገን እንደ አንተ የሚያረጋጋ የለም
እኔም አውቄና አምኜ ይህን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃልህን አሰማኝ"
               መልክአ ቅዱስ ገብርኤል


#መዝሙሩን ለመመልከት ይህንን ይጫኑት





መልካም ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
166 viewsfre የበዓታ, edited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 05:15:23 https://vm.tiktok.com/ZMN74uNEc/
288 views law of Dentistry℅, 02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 04:41:35

191 views law of Dentistry℅, 01:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:31:54
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ዘዳ 33:26

ሁሌ ተበዳይ እርሱ
ተበድሎም የሚክስ እርሱ

ጀርባ የምንሰጠው እኛ
በፍቅር የሚቀርበን እርሱ

የለም ተብሎ የሚካድ እርሱ
እንደ በደላችን ያልከፈለን እርሱ

ከህይወት ይልቅ ሞትን መርጠን የራቅነው ከርሱ
ለሙት ማንነታችን ህይወት ሰጥቶ ያፈቀረን እርሱ

የረሳነው እኛ ያስታወሰን እርሱ

የገደልነው እኛ ያስነሳን እርሱ

በምርጫችን የጠፋነው እኛ በነፃ የፈለገን እርሱ

የተሸከመን እርሱ የከበደን እኛ

ኧረ እንዳንተስ የለም ተመስገን ለዘለዓለም



#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
153 viewsfre የበዓታ, edited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:52:28 #ድንግል_ሆይ_የአንቺ_ሥጋ_ይገርመኛል!!

#ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ  ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ  ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ፤ ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን  ይዘጋዋል፤ አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ  የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን  ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ።  ለዚህ ቃል የለም ዝምታና  አንክሮ እንጂ..

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። ትንሣኤሽን የሚያምን ሁሉ አሜን ይበል።

ምልጃሽ ኢትዮጵያን ይታደግ፤ ለዓለም ምህረት ይሁን!!!

መልካም ዕለት

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
168 views law of Dentistry℅, 05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 18:00:09
#ትንሳኤሽ_ሳይሆን_ሞትሽ_ይደንቀናል!

"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል። የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም! ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም! ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና።

#እመቤቴ_ሆይ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም፤ እንደ ዮሐንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ፤ የዮሐንስ ፀጋ ግን የለኝም!

#እናቴ_ሆይ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ ዓይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና፤ አዝናለሁ! ኤልሳዕ በፀሎት ኃይል የግያዝን ዓይን እንዳበራ፤ አንቺም ዓይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ኃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

#ድንግል_ሆይ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም፤ በልጅሽ መሠረትነት የታነፅኩኝ፤ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ። ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ!! የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"

“የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” 2ኛ ቆሮ 13፥14


መልካም ምሽት

            #ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)


የራማው ልዑል  ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም!
ቤተሰብ ይሁኑ በቴሌግራም ቻናላችን
Join https://t.me/+VgSv2n8UfePFOYVr
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
https://t.me/DNEsuba/1924
206 views law of Dentistry℅, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:55:50
#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_16_በዓለ_ቅድስት_ኪዳነምህረት


✥✥✥ #ሥርዓተ_ነግሥ ✥✥✥
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

✥✥✥ #መልክአ_ሥላሴ ✥✥✥
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል ፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል ፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ወታስተሥርዩ ኃጥያተ ህዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኲኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ፤
ለሕይወት ዘለዓለም ፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፤
ኦ መድኃኒተ ኩሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት።

✥✥✥ #ነግሥ ✥✥✥
እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን ፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳከዊሁ ብርሃን ፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን ፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን ፤
ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን ፤
እመቅድሐ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን ወውስቴታ ተሠርዓ ቁርባን።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፤
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን ፤
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጉላት ፤
ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ ፤
እንተ ሠረፀት ለሕይወት።

✥✥✥ #መልክአ_ኪዳነምህረት ✥✥✥
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ዘተሐደሰ ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቁዓኪ አንሰ ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚዓየ ነፍሰ ፤
እስመ በሥራያ ይዕቲ ቀብዓተኒ ፈውሰ።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ ፤
ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ ፤
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ ፤
ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።

✥✥✥ #ወረብ ✥✥✥
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ/፪/
በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ/፪/

✥✥✥ #መልክአ_ማርያም ✥✥✥
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ ፣
እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ ፣
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ ፣
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ ፣
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ፤
ወልድኪ ይጼዉዓኪ፤
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር።

✥✥✥ #ወረብ ✥✥✥
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት/፪/
"ወልድኪ"/፪/ይጼዉዓኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር/፪/

✥✥✥ #መልክዓ ማርያም ✥✥✥
ሰላም ለእስትፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት ፤
ከመ መዓዛ ዕፀ ኅሩይ ዘውስተ ገነት ፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት ፤
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት ፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ፤
ወኵሉ ነገራ በሰላም።

✥✥✥ #ወረብ ✥✥✥
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ/፪/
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል/፬/

✥✥✥ #መልክአ_ፍልሰታ ✥✥✥
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ ፤
ወዘኢይነጸፍ ባሕርየ ተውዳሱ ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ ፤
ማርያምሰ በምድር ታንሶሱ።

✥✥✥ #ዚቅ ✥✥✥
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማሕደረ መለኮት ፤
እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ፤
ሰማያዊት እንተ በምድር ታንሶሱ።

✥✥✥ #አመላለስ ✥✥✥
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት/፪/
ጽርሕ ንጽሕት ማሕደረ መለኮት/፪/

✥✥✥ #ምልጣን ✥✥✥
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ፤
ኀደረ ላዕሌሃ ፤ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፤
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ።

✥✥✥ #አመላለስ ✥✥✥
ፀቃውዕ ይውኅዝ/፪/
ይውኅዝ እምከናፍሪሃ/፬/

✥✥✥ #ወረብ ✥✥✥
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ/፪/
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ/፪/

✥✥✥ #እስመ_ለዓለም ✥✥✥
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት ፤
እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን ፤
መዓዛ ዕፍረትኪ እምኲሉ አፈው ፤
እትፌሳሕ ወእትሐሠይ ብኪ ፤
ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን ፤
ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኵለንታኪ ሠናይት እንተ እምኃቤየ ፤
ማ፦ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ፤
ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት።

✥✥✥ #አመላለስ ✥✥✥
አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ/፪/
ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት/፬/

✥✥✥ #ወረብ ✥✥✥
"በአልባሰ ወርቅ"/፪/ዑፅፍት ወኁብርት/፪/
እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ/፪/

✥✥✥ #ሰላም ✥✥✥
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ፤
ወኵሉ ነገራ በሰላም።

218 viewsfre የበዓታ, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:32:47 https://youtube.com/shorts/8ONoI4HtTtE?feature=share
196 views law of Dentistry℅, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:52:53 Ethiopia Orthodox Tewahdo Church; New Ethiopia Orthodox Tewahdo 2021 ከኛ ጋር ቤተሰብ ለመሆንና በየቀኑ የሚለቀቁትን መንፈሳዊ መዝሙሮችን ፣ ስብከቶች ለማየት subscribe ያድርጉ !

Ethiopia Orthodox Tewahdo 

#መዝሙሩን ለመመልከት ይህንን ይጫኑት



169 viewsአለም ወለተ ማርያም እግዚአብሔር ሆይ መጀመሪያየ ምንም ይሁን መጨረሻዬን አሳምርልኝ, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ