Get Mystery Box with random crypto!

🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

የቴሌግራም ቻናል አርማ dmtse_tewaedo — 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤
የቴሌግራም ቻናል አርማ dmtse_tewaedo — 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤
የሰርጥ አድራሻ: @dmtse_tewaedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.61K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለናንተ ይሁን channel አችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲሆን ስብከት እና ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡበት የተለያዩ ስብከቶች እና መንፈሳዊ ትረካ በvoice የሚያገኙበት ነው ለመቀላቀል 👇👇

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ ጋር ይሁን

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-10 23:56:35
እንኳን ከዘመነ ማርቆስ
ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችሁ
2015 የሀዘን ሳይሆን የደስታ ዜናን እምንሰማበት
ከክፉ ምኞት በስተቀር ምኞታችን እውን እሚሆንበት ያድርግልን
677 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 07:16:30 ጳጉሜ ለምን እንጠመቃለን?
ቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
762 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 13:16:46

627 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 01:55:20 እመቤታችን ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ 15 ዓመት ቀረው ማለት ነው:: እግዚአብሔር ከሴት የተወለደ ልጁን ሊልክ የዘመኑ ፍጻሜ ቀረበ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር።
ቀድመው ልጅ ቢወልዱ ኖሮ ይህችን የፍጥረት ደስታ የሆነች ልጅ አይወልዱም ነበር:: የእርስዋ የልደት ቀን የፍጥረት ደስታ ቀን ነው::

ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጭዋ የፈለቀችበት ዕለት ነው።

ክርስቶስ መድኃኒት ከሆነ ዛሬ የመድኃኒቱ ሙዳይ የተገኘችበት ዕለት ነው::

ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። በእመቤታችን መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? የእመቤታችን ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል።

እኛም በሊባኖስ ተራሮች (አድባረ ሊባኖስ) መወለድዋን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶችዋ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (በግሪኩ ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን። የልደትዋ ቀን ልደታችን ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
3.3K views22:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 01:54:31 አስር ጊዜ ከመጮኽ ይልቅ አንድ ጊዜ መጸለይ ዋጋ አለው።
ፈርኦንን ከነወታደሩ በቀይባህር ያሰጠመው የራሄል እንባ ነው። ቀይባህርን የከፈለው የሙሴ ጸሎት ነው።
ዳዊት ጎልያድን የገደለው አምላኩን ስለተማመነ ነው። ፍየል ነብር ሲያንቃት ትጮኻለች ። ጓደኞቿም ይጮኻሉ።
ስለጮኹ ነብሩ አይተዋቸውም። በገደላቸው ቁጥር ወኔ ይሰማዋል። ሌላ ይገድላል። ይጮኻሉ፤ ይሞታሉ ። አሁንም ይጮኻሉ ፤ይሞታሉ።
ከዚህ ለመዳን እንደ ራሄል ማንባት፣ እንደ ሙሴ መጸለይ፣ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ማመን ይጠይቃል።
እግዚአብሔር እንባችንን ያብስልን
ከሱ ውጪ መፍትሄ የለንም
2.3K views22:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 18:40:13 ++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
2.3K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:27:13 #ይፍቱኝ_አባ

"የንስሀ መጀመርያ እየሰሩ ካሉት ኃጥያት መለየት ነው"
ፈገግ ብለው ትምህርት የሚያገኙበት ድንቅ ወግ
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
1.6K viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ