Get Mystery Box with random crypto!

🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

የቴሌግራም ቻናል አርማ dmtse_tewaedo — 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤
የቴሌግራም ቻናል አርማ dmtse_tewaedo — 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤
የሰርጥ አድራሻ: @dmtse_tewaedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.61K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለናንተ ይሁን channel አችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲሆን ስብከት እና ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡበት የተለያዩ ስብከቶች እና መንፈሳዊ ትረካ በvoice የሚያገኙበት ነው ለመቀላቀል 👇👇

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ ጋር ይሁን

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-26 08:14:00 ✞ የመስቀል እንቅፍት ተወግዷል ✞
(ገላ 5፥11)
የዓለምን መድኃኒት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በምቀኝነት ሰቅለው ፤ከገደሉት በኃላ ሕግ መተላለፍቸውንና አንዳች በደል ያልተገኘበትን ጌታ በመግደላቸው ሕግ ተላልፈው ጻድቁን ገደሉት ይሉናል በማለት እና የመስቀሉን ተአምራት በማየት ክርስቲያኖችን እንዳይድኑበት መሰቀሉን ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት። ጌታችን ክብር ምስጋና ይድረሰው እና በደል ሳይኖርበት ዓለምን ለማዳንና የሰው ልጅ ሁሉ ከኃጥያት እና ከበደል ነፃ ለማድረግ ሲል እንደ በደለኛ ከአመፀኞች ጋር ተቆጥሮ አይሁድ በግፍ በሰቀሉት ጊዜ ክቡር አካሉ ያረፈበትን እጅ እግሩ በችንካር ጎኑ በጦር ተወግቶ ደሙ የፈሰሰበት መበሆኑ ከዕፀዋት ሁሉ የላቀ ክብርና ሞገስ ያለው ቅዱስ ነው ።

የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ ያከበረው በቅዱስ ስጋው የቀደሰውና መለኮታዊ ኃይሉና ባሕርያዊ ሕይወቱ ያረፈበት ስለሆነ ኃይልና የጥበቡ መገለጫ ነው ። ጌታ ከትንሳኤውና ከዕርገቱ በኋላ ድውያንን በመፈወስ ሙታንን በማስነሳት አንካሶችን ዕውራንን በማዳን ተአምራቱንና ኃይሉን መግለጽ የጀመረውም በቅዱስ መስቀሉ ነው። ከዚህ የተነሳ የዳኑትና ይህን ድንቅ ተአምር የተመለከቱ ሁሉ ሕይወትና ቤዛ የመሆን ጸጋ የተሰጠው መሆኑን እያመኑ መስቀል ኃይላችን መስቀል ቤዛችን የነፍሳችን መድኃኒት ነው እያሉ የጸጋ የአክብሮት ስግደት የሚሰግዱለት ሁነዋል ።

( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዩም አዲሱ ላቀው)



ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
42 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 07:43:15 “እናት ልጇን ዳዴ ስታስለምደው አስቀድማ እጁን ትይዘዋለች፡፡ እንዲሄድም ታደፋፍረዋለች፡፡ ትንሽ መሄድ ሲጀምር ትለቀዋለች፡፡ ትልቀቀው እንጂ ልቧ ሐሳቧ ሁሉ ግን ከልጇ ጋር ነው፡፡ ሊወድቅ ሲል ፈጠን ብላ ትደግፈዋለች፡፡

እግዚአብሔርም ለእኛ ለልጆቹ እንደዚህ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእኛ እይታ ክፉ በሚመስሉ ሁኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፤ ወርቅ ወርቅነቱ ይታወቅ ዘንድ በእሳት እንዲያልፍ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደዚያች እናት በቅርብ ርቀት ሆኖ ይከታተለናል፡፡ ሐሳቡ ልቡ ሁሉ ከእኛ አይለይም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን መልሶ ያነሣናል፡፡ እዚህ ጋር መጠንቀቅ ያለብን ቢኖር በዚሁ የልምምድ ጊዜ ሰይጣን ያንን ሁናቴ ተጠቅሞ በክፉ ዐይን እንድናየው እንዳያስደርገን ብቻ ነው፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሼር ያድርጉ
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
143 views04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 21:47:17 Channel photo removed
18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 14:21:44
ድንቅ ማብራሪያ ነው አድምጡት
761 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 09:42:54 ባህረ ሃሳብ 2015 ዓ.ም

በመርጌታ አምሮ

አዋጅ
አዋጅ
አዋጅ
ዘመነ ማርቆስ ተሻር
ዘመነ ሉቃስ ተሾመ

https://t.me/dmtse_tewaedo

https://t.me/dmtse_tewaedo

https://t.me/dmtse_tewaedo

390 viewsedited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 09:36:14 ርግብ፡-

የመንፈስ ቅዱስ (ማቴ 3፥16) ፤

የእመቤታችን (ዘፍ 8፥8-11) ምሳሌ ሆና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጽፋ እናገኛለን፡፡

ርግብ በአንድ ባል ጸንታ የምትኖር ባሏ የሞተ እንደሆነም ምላሷን ሰንጥቃ በብቸኝነት ትኖራለች፡፡

ሌላ ወንድ የመጣባት እንደሆነ የተሰነጠቀ ምላሷን በማሳየት ትመልሰዋለች፡፡

በርግቦች ዘንድ ድጋሜ ሌላ ወንድ ማግባት ነውር ነው፡፡

ትንሣኤ ሙታን ያለን እኛስ? አስቡት እንኳን የትዳር አጋራችን ሞቶብን ቀርቶ በሕይወት እያሉ በላያቸው ላይ የምንነግድባቸው ቀላል ነን እንዴ?

ርግብን ማስተዋል ከቻልን በሥጋና ደሙ ጋብቻችንን መሥርተን በአንድ ጸንተን በመተሳሰብ፣ በመረዳዳትና በመፈቃቀር የምንኖር እንሆናለን፡፡

ምናልባት በሞት የምንለያይ ከሆነና ብቻን ለመኖር አስቸጋሪ ሆኖ ከተገኘ በድጋሜ በሥጋና ደሙ ማግባት ይቻላል፡፡

ይህ ሥርዓት የሚፈጸመው ለምዕመናን ሦስት ጊዜ ለካህን ሁለት ጊዜ (ክሕነቱ ፈርሶ) ከዚህ የዘለለ ጋብቻ ግን ከዝሙት ይቆጠራል፡፡

ስለዚህ ከርግብ በመማር ለትዳራችን ታማኝ በመሆን እግዚአብሔርን በመፍራት ልንኖር ይገባናል፡፡
933 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 15:29:38
የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡
በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ? ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡ በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡ በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡
በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡ በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡ ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡
በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡ በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡
ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ? መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡
መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ጌጥ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡
403 views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 07:11:41

299 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 10:34:34 "ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡ ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል። እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ሰማዕትነት አያምልጣችሁ"

ቀናችንን የፍቅር የመዋደድ እናድርገው! መልካም ለሊት ይሁንላችሁ!

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
418 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ