Get Mystery Box with random crypto!

✞ የመስቀል እንቅፍት ተወግዷል ✞ (ገላ 5፥11 | 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

✞ የመስቀል እንቅፍት ተወግዷል ✞
(ገላ 5፥11)
የዓለምን መድኃኒት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በምቀኝነት ሰቅለው ፤ከገደሉት በኃላ ሕግ መተላለፍቸውንና አንዳች በደል ያልተገኘበትን ጌታ በመግደላቸው ሕግ ተላልፈው ጻድቁን ገደሉት ይሉናል በማለት እና የመስቀሉን ተአምራት በማየት ክርስቲያኖችን እንዳይድኑበት መሰቀሉን ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት። ጌታችን ክብር ምስጋና ይድረሰው እና በደል ሳይኖርበት ዓለምን ለማዳንና የሰው ልጅ ሁሉ ከኃጥያት እና ከበደል ነፃ ለማድረግ ሲል እንደ በደለኛ ከአመፀኞች ጋር ተቆጥሮ አይሁድ በግፍ በሰቀሉት ጊዜ ክቡር አካሉ ያረፈበትን እጅ እግሩ በችንካር ጎኑ በጦር ተወግቶ ደሙ የፈሰሰበት መበሆኑ ከዕፀዋት ሁሉ የላቀ ክብርና ሞገስ ያለው ቅዱስ ነው ።

የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ ያከበረው በቅዱስ ስጋው የቀደሰውና መለኮታዊ ኃይሉና ባሕርያዊ ሕይወቱ ያረፈበት ስለሆነ ኃይልና የጥበቡ መገለጫ ነው ። ጌታ ከትንሳኤውና ከዕርገቱ በኋላ ድውያንን በመፈወስ ሙታንን በማስነሳት አንካሶችን ዕውራንን በማዳን ተአምራቱንና ኃይሉን መግለጽ የጀመረውም በቅዱስ መስቀሉ ነው። ከዚህ የተነሳ የዳኑትና ይህን ድንቅ ተአምር የተመለከቱ ሁሉ ሕይወትና ቤዛ የመሆን ጸጋ የተሰጠው መሆኑን እያመኑ መስቀል ኃይላችን መስቀል ቤዛችን የነፍሳችን መድኃኒት ነው እያሉ የጸጋ የአክብሮት ስግደት የሚሰግዱለት ሁነዋል ።

( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዩም አዲሱ ላቀው)



ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet