Get Mystery Box with random crypto!

“እናት ልጇን ዳዴ ስታስለምደው አስቀድማ እጁን ትይዘዋለች፡፡ እንዲሄድም ታደፋፍረዋለች፡፡ ትንሽ መ | 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

“እናት ልጇን ዳዴ ስታስለምደው አስቀድማ እጁን ትይዘዋለች፡፡ እንዲሄድም ታደፋፍረዋለች፡፡ ትንሽ መሄድ ሲጀምር ትለቀዋለች፡፡ ትልቀቀው እንጂ ልቧ ሐሳቧ ሁሉ ግን ከልጇ ጋር ነው፡፡ ሊወድቅ ሲል ፈጠን ብላ ትደግፈዋለች፡፡

እግዚአብሔርም ለእኛ ለልጆቹ እንደዚህ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእኛ እይታ ክፉ በሚመስሉ ሁኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፤ ወርቅ ወርቅነቱ ይታወቅ ዘንድ በእሳት እንዲያልፍ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደዚያች እናት በቅርብ ርቀት ሆኖ ይከታተለናል፡፡ ሐሳቡ ልቡ ሁሉ ከእኛ አይለይም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን መልሶ ያነሣናል፡፡ እዚህ ጋር መጠንቀቅ ያለብን ቢኖር በዚሁ የልምምድ ጊዜ ሰይጣን ያንን ሁናቴ ተጠቅሞ በክፉ ዐይን እንድናየው እንዳያስደርገን ብቻ ነው፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሼር ያድርጉ
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet