Get Mystery Box with random crypto!

አDINU- NESIHA

የቴሌግራም ቻናል አርማ dinisnesiha — አDINU- NESIHA
የቴሌግራም ቻናል አርማ dinisnesiha — አDINU- NESIHA
የሰርጥ አድራሻ: @dinisnesiha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

قال ﷺ ' الدين النصيحة قلنا لمن؟ قال لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم....
رواه مسلم
ዲን መመካከር ነው።
ኑ እንተዋውስ።
ለአስተያየት. @Umu_Hajer

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-05 13:08:50
266 viewsوَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِ, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:45:31
➪ልጆችህ ሷሊህ ሊሆኑልህ ትፈልጋለህ?
➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮➮

➧አራት መስፈርቶችን ከቁርዓን ተቀበለኝ

እራስህን ከምንም በፊት ቀድመህ ሷሊህ አድርግ፦

﴿وكان أَبُوهُمَا صالحا﴾
አባታቸው ሷሊህ ነበር

አሏህ ሆይ ልጆቼን ሷሊህ አድርግልኝ ብለህ ዱዓ አድርግላቸው፦
﴿وأصْلِحْ لي في ذُرِّيَّتِي ۖ﴾
➮ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ

ሰላትን በመሃላቸው አስተካክለህ ስገድ፦

{رَبِّ ٱجْعَلْنِى مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۚ }

«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡

ሰይጣን እንዳይቀርባቸው በአሏህ ጠብቃቸው፦

{َ وَإِنِّىٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيْطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ}

እኔም እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» አለች፡፡

☞︎︎︎ ይህን ምክሬን ከሰማሃኝ ቦሃላ እንዲህ በል፦

رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَآءِ
ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
1.4K viewsوَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِ, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:10:56 በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::

የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"

አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።

በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::

አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!
263 viewsوَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِ, 15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ