Get Mystery Box with random crypto!

አDINU- NESIHA

የቴሌግራም ቻናል አርማ dinisnesiha — አDINU- NESIHA
የቴሌግራም ቻናል አርማ dinisnesiha — አDINU- NESIHA
የሰርጥ አድራሻ: @dinisnesiha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

قال ﷺ ' الدين النصيحة قلنا لمن؟ قال لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم....
رواه مسلم
ዲን መመካከር ነው።
ኑ እንተዋውስ።
ለአስተያየት. @Umu_Hajer

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:32:50 በሴት ልጅ መንገድ ላይ እሾህ አታስቀምጥ! እህትህ በዛ መንገድ ላይ ባዶ እግሯን ትመጣ ይሆናልና።

እያሰባችሁ!!!!!
@DinisNesiha
273 views. ...., 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:12:22 كتاب التوحيد
ኪታቡ ተውሒድ ክፍል 1
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

https://t.me/DinisNesiha
70 viewsكوني مع الله يكون معكي, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:48:53 ሶላትን ከወቅቱ አሳልፈው ለሚሰግዱ


ጥያቄ


ለኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ተብለው ተጠየቁ።

አንዳንዴ ሶላትን ከወቅቱ አሳልፋለሁ። ይህ የማደርገው በመዘናጋት ሳይሆን የቤት ስራ ስለሚበዛብኝ ነው። በዚህ ስራዬ ወንጀል አለብኝ?

መልስ


አዎ ወንጀል አለብሽ። አንድ ሰው የሶላትን ወቅት ሊያሳልፍ በፍፁም አይፈቀድለትም። ሶላት ከኢስላም ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው። አላህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል፦ ((ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናት፡፡ ((ሱረቱ አል-ኒሳእ - 103)) ስለዚህ አንድ ሰው ሶላቱ በትክክለኛው ወቅት ሊፈፅመው ይገባል። ምመክርሽ ነገር ቢኖር፦ ሶላትሽ በትክክለኛው ወቅት መስገድሽ በስራሽ የአላህ እገዛ ታገኛለሽ። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል፦ ((በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ (አል-በቀራህ - 45))
[فتاوى سؤال على الهاتف. (المجلد الثاني السؤال (٦٧٠)]
166 views. ...., 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:30:41 ማንነትክን በወሬ ሳይሆን በተግባር አሳይ!!

" الكلماتُ قد تكذب !
لكن التصرفات دائماً تقولُ الحقيقة "

ንግግር ሊዋሽ ይችላል
ድርጊት ግን ሁሌም እውነትን ይመሰክራል።
111 views. ...., 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:03:47 ☞«ነገሮች እንዳይሳኩልን ከሚያደርጉና በስኬት ፊት ከሚቆሙ እንቅፋቶች መካከል አንደኛው ወንጀል ነው» ይላሉ ኢማም ኢብኑል ቀይም።

⇛አንድን ሀሳብ ለማሳካት ተነስቶ በተደጋጋሚ ሞክሮ አልሳካለት ያለ ሰው ሱስ የሆነበት ያልተላቀቀው ኃጢአት አለና እሱን ይተው ይላሉ ዑለሞችም።

ቆንጆ ምሽት
186 views. ...., 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:53:03 رياض الصالحين
ሪያዱ ሷሊሂን ክፍል 6

በሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር
 https://t.me/DinisNesiha
178 viewsكوني مع الله يكون معكي, 05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:36:34 ጥቂት ነጥቦች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ
~
1.  ወገኔ ሆይ! አገርህን አትልቀቅ።

ባለፈው ተፈናቃዮች ላይ የደረሰውን አስታውስ። ደብረ ብርሃንና ባህርዳር ለተፈናቃዮች ከማጎሪያ ካምፕ የማይለዩ እንደነበሩ ሲወራ ነበር። አሁን ደግሞ ነገሮች ከቀድሞው ቢብሱ እንጂ የተሻሉ አይደሉም። ፖለቲከኛውን ተወው። ህዝብ እራሱ ኑሮ ስለከበደው ሊጨካከን፣ ሊሰላች ይችላል። ሩቅ አትሂድ። ደሴ ወልዲያን፣ ወልዲያ ቆቦን ሊሰለች ይችላል። የጎደለበት ደግሞ በትንሽ በትልቁ ይከፋዋል። ስለዚህ በተለየ እፈለጋለሁ ብሎ የሚሰጋ ካልሆነ በስተቀር ጦርነቱ ቀጥታ ከሚካሄድባቸው ቀጠናዎች ለጊዜው ዞር ከማለት ውጭ ካገር ርቆ መሄድ ስቃዩን የከፋ ያደርገዋል።

2.  ወገኔ ሆይ! ንብረትህን ጠብቅ።

ሩቅ ብቻ አትመልከት። እዚያው በዙሪያህ ለዘረፋ ተደራጅተው ከግለሰብ ንብረት እስከ ተቋም ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ዛሬም ይኖራሉ። ፍሪጅና ቴሌቪዥን ሳይቀር በግመል እየጫኑ የወሰዱ የገጠር ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። “መብራት የላችሁ ምን ያደርግላችኋል?” ሲባሉ “እንሸጠዋለን” ሲሉ ነበር። ስለዚህ ቅድሚያ ለህይወት ጥንቃቄ ካደረግክ በኋላ በቅርብህ ሆነህ በተቻለህ መጠን ንብረትህን ተደራጅተህ ጠብቅ።

3.  ወገኔ ሆይ! ለፈተና እራስህን አዘጋጅ!

ወደድንም ጠላንም ፈተና ላይ ነው ያለነው። መጠኑ ከህዝብ ህዝብ በእጅጉ እንደሚለያይ ግልፅ ነው። ፈተናው ምን ያህል እንደሚዘልቅም አናውቅም። የሆነች ያክል የምንዘጋጅባት ሰበብ ካለችን ባለችን መጠን ለሚመጣው ሁሉ ራሳችንን እናዘጋጅ። ምግቡ፣ ወፍጮው፣ ባንኩ፣ መብራቱ፣ ቴሌው፣ መድሃኒቱ፣ ... ብዙ ነገር ይቸግራል። እስካሁንም ብዙ የተፈተነ አለ። ልዩነቱ ብዙ ባይሆን እንኳ የተዘጋጁበትና የተዘናጉበት ፈተና አንድ አይደለም። አላህ ለሁሉም ፈረጃውን ያቅርብልን።

4.  ወገኔ ሆይ! ጊዜ አይተህ አትለወጥ!

ለሚያልፍ ቀን ትዝብት ላይ አትውደቅ። የትኛውም ቡድን አጠቃኝ በሚል ማመሃኛ ማንንም ብሄር ለይተህ እንዳታጠቃ። የአማራ ህዝብ ሆይ! ህወሓትን መነሻ አድርገህ ለፍቶ አዳሪ ትግሬን አታጥቃ። “ያው ናቸው” ከሚል ስሜት ወለድ ሂሳብ ራቅ። “ህወኃት እከሌን አካባቢ የተቆጣጠረው ተፈናቃይ ትግሬዎችን ተጠቅሞ ነው” እየተባለ የሚናፈሰው ብታምንም ባታምንም ከንቱ ውሸት ነው። እንዲህ አይነት አሉባልታ ይዘህ ደካሞችን እንዳትጎዳ።
ትግሬው ሆይ! ህወኃት ሲገባ ጠብቀህ አደባባይ ለጭፈራ አትውጣ። ጠቋሚ፣ አፋኝ፣ አሳፋኝ ለመሆን አትሞክር። ሃይማኖት ወይም ሞራል እንኳ ባይገታህ ቢያንስ ለራስህ ፍራ! ነገሮች የተቀያየሩ እለት መግቢያ ታጣለህ። በባለፈው ግጭት አማራውም፣ ትግሬውም፣ ኦሮሞውም፣ አፋሩም ዘንድ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲወሩ ነበርና አላህን ልንፈራ ይገባል።

5.  ወገኔ ሆይ! ለመጣ ለሄደው አታጨብጭብ።

አንድ ኃይል አንድን አካባቢ ሲቆጣጠር ሆ ብሎ መውጣት፤ ሌላው በግሩ ሲተካ አሁንም ሆ ብሎ መነሳት ይሄ ግልብነት ነው። የሃገራችን ፖለቲካ ቂመኛና ተበቃይ ነው። እንኳን የገባበትን፣ የሌለበትንም ጊዜ ተጠግቶ ያጠቃል። ደግሞም በጣም ተገለባባጭ ነው። እዚች አገር ውስጥ ስንት አይሆንም የተባለ ነገር ሆኗል! መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ህወኃት ዳግም ያንሰራራል ብሎ የገመተ አልነበረም። ህወኃት ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ ይመለሳል ብሎ የገመተም አልነበረም። ስለሆነም ጥንቁቅ መሆን ያስፈልጋል። በሁለቱም አይንህ ዛሬ ላይ ብቻ አታፍጥጥ። በአንድ አይንህ ነገን ተመልከት።

6.  ወገኔ ሆይ! ህይወት አትርፍ።

አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የሚጠሉትን ለማጥቃት የማያመነቱ እርኩስ ፍጡሮች ይኖራሉና ቢቻልህ ያለ ጥፋታቸው የበደለኞች ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ወገኖችን አትርፍ። ከጎናቸው ቁም። በባለፈው ግጭት ህወኃት ሲገባ ጠብቀው ደካሞችን ያጠቁ ሰዎች አሉ። ከነሱ አንፃር ሲታይ ህወኃት በጣም የተሻለ ነበር። መረጃ ያለው ሰው የምለው ይገባዋል። ህወኃት ከወጣ በኋላም እንዲሁ ከየትኛውም ኃይል ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ምስኪኖች ተጎድተዋል። ከተቻለን ጊዜ አይተው ከሚያጠቁ ነውረኞች አንድ ነፍስ እንኳ ብናተርፍ ዋጋው የትና የት ነው!! በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ በነበረውን ግጭት የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ኦሮሞዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። አማራ ውስጥ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ትግሬዎችን ያተረፉ ስንት አማራዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ትግሬዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት!

7.  ወገኔ ሆይ! ወቅታዊ ግጭቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሃይማኖት ጋር እንዳታጠላልፍ።

የየትኛውም ቡድን ደጋፊ ልትሆን ትችላለህ። የኔ የምትለው ወገን ከሌሎች በተለየ እንደተገፋ ሊሰማህ ይችላል። ግን እወቅ! ሌሎችም መሰል ህመም አላቸው። ቢቻል በፖለቲካውም ሞራል ግብረ ገብነት ቢኖርህ እሰየው። ያለበለዚያ ግን የሃይማኖት ተቋማትም፣ አስተማሪዎች እና የደዕዋ መድረኮችም አንተ በምትፈልገው መልክና መጠን እንዲያወሩ፣ የፖለቲካ ፍጭቶች ማራገፊያ እንዲሆኑ አትፈልግ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ሆነ መሬት ላይ እየተከተልክ በአክቲቪስት ቋንቋ እንዲያወሩ አጉል አትወትውት። ልትረዳ ቢያቅትህ ቢያንስ አደብ ይኑርህ። ከፖለቲከኛ ጋር የለመድከውን እሰጥ አገባ በየደረስክበት አትድፋ።

8. የሃይማኖት አስተማሪ ሆይ! ከመንጋው ተለይ!

ብሄርህን ተከትለህ ቅስቀሳ ውስጥ አትግባ። ሌላው አካል ለጦር ቢቀሰቅስ አንድ ሁለት ነገር ተመልክቶ ነው። አንተ ተጨማሪ አርቀህ የምትመለከትበት አላህን መፍራቱ ሊኖርህ ይገባል። ያለበለዚያ በምንህ ነው ከሌሎች የምትለየው? ኢን ሻአላህ ነገ ሰላም ይመጣል። እሱን ታሳቢ አድርግ። መንጋው ሊያግባባህ፣ ሊገፋፋህ፣ አልሆን ሲለው ሊያወግዝህ ይችላል። የፈለገውን ይበል እሱ በቀደደው አትፍሰስ። የሃይማኖት አስተማሪ ሆነው በቀጥታ የግጭት ተሳታፊ፣ ወይም ቀስቃሽ፣ ወይም ደጋፊ፣ ወይም የዘር ጥላቻ ጠማቂ የሆኑ መርዘኛ ሰባኪዎች ሁሉም ብሄር ጋር አሉ። እነዚህ አካላት ነገ ችግሩ ቢያልፍ እንኳ የማያልፍ ጠባሳ እየጣሉ ነው። ጦሳቸውም ከራሳቸው አልፎ ለህዝብ ይተርፋል። ከሃይማኖትህ ተማር። እስካሁን ካለፈው ተማር። ከሌሎች ድክመት ተማር። የትኛውንም ውሳኔ ብትመርጥ ከትችት ላታመልጥ ነገር የሰው ስሜት ተከትለህ እንዳትወስን። አላህን አስብ።
በመጨረሻም አደራ የምለው እንተዛዘን፣ እንተሳሰብ፣ ዱዓእ እናድርግ፣ ወደ ጌታችን እንመለስ። አላህ ከገባንበት መከራ አውጥቶ የሰላም አየር የምንተነፍስ ያድርገን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
105 views. ...., 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:03:30 ዒማሙ አህመድ መሆን ካቃተህ
አቡል ኸይሰም ሁን

የታላቁ ዒማም አህመድ ዒብኑ ኸንበል ልጅ የሆነው አብደሏህ እንዲህ ሲል ይተርካል;

አባቴ ብዙ ጊዜ "አላህ ሆይ ለአቡ ኸይሰም ማረው, ለአቡል ኸይሰም ዕዘንለት" ሲል እሰማው ነበር።

አባቴ ሆይ አቡል ኸይሰም ማን ነው ብዬ ጠየቅኩት

"ከገጠሬዎች የሆነ አንድ ሰው ነው ፊቱን ራሱ አይቼው አላቅም።
ግን እነዝያ ያለፉት በሆኑ ስገረፍባቸው በነበሩት ሌሊቶች ውስጥ አንድ ቀን መግረፊያ ክፍል አስገብተው አስቀመጡኝ ሳለሁ; የሆነ ሰው ጀርባዬን መታ አረገኝና => {አህመድ ዒብኑ ኸንበል አንተ ነህን } አለኝ
አዎን አልኩት
=> {ታቀኛለህን }ሲለኝ
አላቅህም አልኩት

{እኔ አቡል ኸይሰም የተባልኩ የገጠር ሰው ነኝ, ኸምር እጠጣለሁ, የሰው ንብረትም ዕቀማለሁ, በዚህ ድርጊቴ መንግስት ፊት ቀርቤ አስራ ስምንት ሺህ ግርፋት በተለያዩ ጊዜያት ተገርፌያለሁ።
ይህ ሁሉ ስገረፍ ግን በሸይጣን መንገድ ላይ ሆኜም እችለው ነበር። አህመድ ሆይ አንተ ግን በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ አለኝ።

ከዝያ በኋላ አስረው ሲገርፉኝ አንዲትን ግርፋት ባረፈችብኝ ቁጥር የአቡል ኸይሰም ንግግር ትዝ ይለኝና በውስጤ
{አህመድ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ } እል ነበርኩ

አህመድ ዒብኑ ኸንበል መሆን ካቃተህ አቡል ኸይሰም ሁን

ምንም እንኳ ውድቅ የሆነ ነገር ላይ የተዘፈቅክ ብትሆንም የዕውነት ባልተቤቶችን ውደዳቸው

ምንም እንኳ በወንጀል የሰመጥክ ብትሆንም ደጋጎችን ውደዳቸው

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@DinisNesiha
┗━ ━━━━ ━┛
928 viewsكوني مع الله يكون معكي, 10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:04:43 ሴት ልጅ የማህበረሰቡ ግማሽ ናት
እሷ ከተስተካከለች ግማሹ ማሀበረ ሰብ ይስተካከላል


መልካም ውሎን ተመኘሁላቹ


@DinisNesiha
268 viewsاللهم صل وسلم عل نبينا محمد, edited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:40:03 እራስህን በመልካም ሰዎች ክበብ ያኔ መልካም ትሆናለህ።

ቆንጆ ቀን
238 views. ...., 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ