Get Mystery Box with random crypto!

ዝሙት በየሜዳው ሲሰበክና ሰዉ ትዳርን እያጣጣለ በዝሙት ሲዘምን እያየን ዝም እንበል! ታዛቢዎትም እ | 🍂 ዲነል ኢስላም 🕌


ዝሙት በየሜዳው ሲሰበክና ሰዉ ትዳርን እያጣጣለ በዝሙት ሲዘምን እያየን ዝም
እንበል! ታዛቢዎትም እንሁን! ዝሙትን ለመከላከል ሁላችንም የምንችለውን ሳይሆን የሚጠበቅበን እናድርግ!

.....አንዱ ትውልድ ዛፍን ሲተክል ሌላው እንደሚጠለልበት ሁሉእንዱ ትውልድ ኃጢአትን ሲዘራ የኃጢአቱ መዘዝ በቀጣዩ ትውልድ ላይ በረጅሙ ጥላውን ያጠልበታል፡፡ በውጤቱም ያኛው የዚኛው ተከታይ ይሆናል፡፡ በፍርዱም ዕለት እርስ በርስ ይረጋገማሉ፡፡ አንዱ አስከታይ ሌላኛው ተከታይ ሆነው ሁለቱም በእጥፍ
ይቀጣሉ፡፡ ይህንኑ ማረጋገጥ ከፈለጉ ሱረቱል አዕራፍ ከ38-39 ያሉትን አናቅጽ ያንብቡ፡፡(Surah Al-A’raf (الأعراف), verses: 38)

قَالَ ٱدْخُلُوا۟ فِىٓ أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِكُم مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ فِى ٱلنَّارِ كُلَّمَا دَخَلَتْ أُمَّةٌ لَّعَنَتْ أُخْتَهَا حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُوا۟ فِيهَا جَمِيعًا قَالَتْ أُخْرَىٰهُمْ لِأُولَىٰهُمْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمْ عَذَابًا ضِعْفًا مِّنَ ٱلنَّارِ قَالَ لِكُلٍّ ضِعْفٌ وَلَٰكِن لَّا تَعْلَمُونَ

«ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡ መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን፡፡ ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች፡፡ (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል፡፡

@Dinel_islam @Dinel_islam