Get Mystery Box with random crypto!

#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን #ጥያቄ | ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

#ጥያቄና_መልስ

ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው

#መልስ ኦርቶ ዶክስ 2 ሁለት ቃል ጥምርት ሲሆን ኦርቶ ማለት ቀጥተኛ ትክክለኛ ማለት ነው። ዶክስ ማለት ደግሞ አመለካከት እምነት ነው ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ቀጥተኛ እና ትክክለኛ ማለት ነው።

ለእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደገና ደካማ ወደ መናቅም ወደ መጀመሪያ ወደ ክህደት ትምርት ለምን ትሄዳላችሁ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሀይለ ቃል የት ይገኛል ም&ቁ ጥቀስ?

መልስ ገላ 4፥9 ላይ ይገኛል።

ኢየሱስ የሚለው ቃል የምን ቃል ነው ትርጉሙስ ምንድነው?

መልስ ከእብራይስጥ የተወረሰ የግሪክ ቃል ነው። ትርጓሜውም #አዳኝ ማለት ነው።

ማቴ 1፥21 ይገኛል።

እስከመጨረሻ የፅና ግን እርሱ ይድናል የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሀይለ ቃል የትላይ ይገኛል?

መልስ ማር 10፥22 ይገኛል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሊቀ,ጳጳስ ማን ይባላል?

መልስ ፋሪ ምናጦስ ወይም አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሀን ይባላል።

ቅዳሴ ማርያምን የፃፈ አባት ማነው?

መልስ አባ ሕርያቆስ ነው።

የትንሳኤ መጀመሪያ ማነው?

መልስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

የመጀመሪያ የብሉይ ኪዳን ሰአሊው ማነው?

መልስ #እግዚአብሔር ሙሴን በታቦተ ህጉ ፅላትን ኪዳኑ ላይ ስዕለ ክሩቤልን እንዲስል አዞት ነበር ስለዚህ ሙሴ ነው የሳለው ኦሪ ዘጽ 25፥19
ኦሪተ ዘጽ 37፥6 ላይ ይገኛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታችን የሳለው ማነው?

መልስ ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው።

የእመቤታችንን ስዕል ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ማነው ?

መልስ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው።

ቅዱሳን መላእክት አንድ ጊዜ የተፈጠሩና የማይባዙ በእለተ---------------የተፈጠሩ ናቸው? ተፈጥሮ አቸውም ከ---------እና በ----------የተፈጠሩ ናቸው??

መልስ በእለተ እሁድ የተፈጠሩ ናቸው .ከሳትና .ከንፋስ. የተፈጠሩ ናቸው መጽሐፈ ኩፋሌ 2፥6፥8 ላይ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስተያን የነገር ማርያም አስተምሮ መሰረት እመቤታችንን ድንግል ማርያም የምትጠራባቸው 3/ ሦስቱ ዋና ዋና ስያሜዎች አሏት እነሱም ምን ምን ናቸው ዘርዝሩ???

መልስ 1ኛ በአማን ንፅህት 2 ኛ ወቅድስት 3ኛ .በኩሉ ናቸው።

እነሆ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሀለሁ ወደዚችም ምድር እመልስሀለሁ የነገርኩህ ሁሉ እስክገለፅልህ አልተውህም ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀይለ ቃል የት ይገኛል የፃፈለት ማነው የተፃፈለትስ ለማን ነው?

መልስ የፃፈው እግዚአብሔር ነው።የተፃፍለት ለያእቆብ ነው ኦሪት 28፥15። ላይ ይገኛል።

እራቁቴን ከእናቴ ማህፅን ወጥቻለሁ እራቁቴን ወደዛ እመለሳለሁ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ያለው ማነው??

መልስ ፃድቁ እዮብ ነው። መጽሐፈ እዮብ 1፥21 ላይ ይገኛል።

ሁሉ ተፈቅዶልኛል ግን ሁሉ አይጠቅመኝም የሚያነፃኝ አይደለም። ይህ ሀይለ ቃል የት ይገኛል??

መልስ 1ኛ ቆሮ 10፥፦፦

ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ቢጠባበቅ ምን አለ ያለው አባት ማነው??

መልስ ነብዩ ኤርሚያስ ነው።

መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ ብሎ በራእይ የተነገረው አባት ማነው???

መልስ አፄ ዘርያእቆብ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር ይፍታ ያለው አባት ማነው።

መልስ አባ ጴጥሮስ ነው።

በእለተ ረቡዕ የተፈጠሩ ፍጥረታት እነማናቸው ??

መልስ ፅሀይ እና ጨረቃ ከዋከብት ናቸው።

የጦቢትን ዓይን ያበራው ማነው???

መልስ ቅዱስ ኡራኤል ነው።

7 ሰባቱ ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉትን ዘርዝሩ ???

1 ሚስጢረ- ጥምቀት
2 ሚስጢረ- ሜሮን
3 ሚስጢረ- ቁርባን
4 ሚስጢረ- ክህነት
5 ሚስጢረ- ተክሊል
6 ሚስጢረ- ንስኃ
7 ሚስጢረ- ቀንዲል

በቅዳሴ ጊዜ 5 አምስት ምስዋቶች አሉ። እነሱን ዘርዝር???

መልስ 1 የቁርባን ምስዋት
2 የከንፈር ምስዋት
3 የመብራት ምስዋት
4 የእጣን መስዋት
5 የሰውነት ምስዋት ናቸው

ቤዛ ማለት ምን ማለት ነው??

መልስ ዋጋ ማለት ነው። ወይም ስለ አንድ ነገር አልፎ የተሰጠ መከታ ማለት ነው።

ቤተ ክርስቴያን 3/ሦስት መቅደሶች አሏት እነሱም ምን ምን ናቸው ዘርዝሩ???

መልስ 1 ቤተ መቅደስ
2 ቤተ ልሄም
3 ቤተ ቅድስት ናቸው።

ጌታችን መድኃኒታችን በመስቀል ላይ በዋለ ጊዜ የተፈጠሩ ታምራቶችን ዘርዝሩ ???

መልስ ፅሀይ ጨልማለች ከዋከብቶች እረግፈዋል መቃብራት ተከፍተዋል የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለ2 ሁለት ተከፍለዋል ጨርቃ ደም መስላለች አለቶች ተሰነጣጥቀዋል ሙታን ተነስተዋል ።

ለመጀመሪያ ካህን ሁኖ የተመረጠው እና ላገልግሎት የተጠራው አባት ማነው??

መልስ መልከ ፃዴቅ ነው
ኦሪት 14፥18

ቤተክርስቲያን ውስጥ በዓመት ስንት አይነት ቅዳሴዎች አሉ???

መልስ 14 ቅዳሴ አሉ።

ፀጋ ሲሰጥህ በተሰጠህ ፀጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ ያለው ቅዱስ አባት ማነው???

መልስ ማር ይሳሀቅ ነው።

እራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪ ጥበብ ይለየዋል ያለው አባት ማነው??

መልስ አባታችን አርጋዊ መንፈሳዊ ።

ፍጡራንን መርምሮን ማውቅ ካልቻልን ሁሉን የፈጠር እርሱን መርምሮ ማውቅ እንደት ይቻላል ያለው አባት ማነው???

መልስ አባ አትናቴወስ ነው።

በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍረዱ ይህን ከጠበቃችሁ እርስቲቱን ትወርሳላችሁ ያለው አባት ማነው??,

መልስ ታላቁ አባ መቃርስ ነው።

ስጋዊ ፍለጓቶችን ማሸነፍ ለአክሊል ህይወት የሚያበቃ #ሰማእትነት ነው ብሎ የተናገርው አባት ማነው??

መልስ ብፁ አቡነ ጓርጓርዮስ ካአል ነው።

የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ #የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ ብሎ የተናገርው አባት ማን ይባላል??

መልስ ብፁ አቡነ ጓርጓርዮስ ነው።

5 አምስቱ ፍኖተ ፃድቅ የተባሉትን እነማናቸው ዘርዝሩ???

መልስ 1ፍቅር
2 ትህትና
3 ጾም
4 ፆሎት
5 ምፅዋት ነቸው።

5 አምስቱ እቀባተ መስቀል የተባሉት እነማናቸው ዘርዝሩ ???

መልስ 1 ጣወትን ማምለክ
2 አፍቅሮ ነዋይ
3 ተጣልቶ አለመታረቅ
4 ሰው መግደል
5 እናት አባትን አለማክበር ናቸው።

5 አምስቱ ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት እነማናቸው ዘርዝሩ ????

መልስ 1 ትንቢት
2 ስስት
3 ምቀኝነት
4 ስርቆት
5 ዝሙት ናቸው

7ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ይሚባሉትን ዘርዝሩ???

መልስ 1ቅዱስ ሚካኤል
2 ቅዱስ ገብረኤል
3 ቅዱስ ፋኑኤል
4 ቅዱስ ራጉኤል
5 ቅዱስ ኡራኤል
6 ቅዱስ ሳቁኤል
7 ቅዱስ አፍኒን

7 ሰባቱን አፅዋማት ዘርዝሩ???

መልስ 1 ዐብይ ፆም
2 የሐዋርያት ፆም
3 የፍልሰታ ፆም
4 የነብያት ፆም
5 የነነዌ ፆም
6 ፆመ ገሀድ
7 ፆመ ድህነት

#ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
#ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን

#የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የቅዱሳን መላእክት ልመናቸው ፀሎታቸው
ፃድቃን ሰማእታት ረደኤት በርከታቸው ከሁላችንም ጋር ይኑር አሜን፫