2021-10-30 22:11:38
ለትዉስታና ለፈገግታ
# እኛ_የ90ዎቹ
እስኪ ልጅነታችንን ወደኃላ መለስ ብለን እንቃኘው የምን ዘመን ልጆች ነበርን? ከነኚ ውስጥ ቢያንስ 20ዎቹ ካላጋጠሙህ አንተ የቼሪ ዘመን ልጅ ሳትሆን የኢትዮጲስ ዘመን ልጅ ነህ። እነሆ ዘና በሉበት
1. እሁድ ጠዎት አበባ ተስፋዬን ለማየት የጓጓን
2. ኮርኪ (ድንጋይ) ደርድረን በድንጋይ በመታ የተጫወትን (ባገረጣ)
3. በማማ ወተት ላስቲክ ኳስ ሰርተን የተራገጥን
4. በFather ካልሲ ጥምጣም ሰርተን ስልክ እንጨት ላይ አስረን የተጫወትን (ቴዘር)
5. የልጆች አለም ቀበጥዎ ድመት, አሊባባ እና አርባዎቹ ሌቦች,ሙሽራዋ አይጥን እያነበብን ያደግን
6. ያይኔ እና ሶስት ወፎች የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ የተከታተልን
7. በSony እና Mayota DVD Contra,super Mario.. የተጫወትን
ቅዳሜ ማታ ታላቅ ፊልም ያየን
8. አስተማሪ እያስተማረ በእስኪርቢቶ ቀፎ በወረቀት የተታፋን
9. በዴክ(VHS) ፊልም እያጠነጠንን የሾፍን አንበሳ ግቢ እና ጊዬን ትልቁ መዝናያችን የሆነ
10. እሁድ ስምንት ሰዓት ጠብቀን 120 እየሳቅን ያየን
11. ዲሽ ሳይሆን አንቴና ለማሽከርከር ጣራ ላይ የወጣን tv africa ያየን
12. በሞዴል ሀያት አህመድ (miss Ethiopia) እና ሄርሜላ ገ/ኪዳን ውበት የተደመምን
13. ባለ ፎቅ የብረት ምሳ እቃ የያዝን
በ16 ደብተር ሉክ የተማርን
በ Bifa,Dollar buget,Bic እስኪርቢቶ የተማርን
14. ፀጉራችንን ቦጆ የተቆረጥን
Mtv ላይ pimp my ride, cribs,Disaster Date,Sweet sixteen ....ያየን
15. በቆርኪ ልጣጭ ቀበቶ የሰራን
በህንድ ፊልም አክተሮች ፗስተር ልዩ አንድ አይነት የተጫወትን
16. ሂፕ ሆፕ,ሳሬም,አብዎለድ ብስኩት የበላን
17. ሰማያዊ እና ቀይ የሆነ ላጲስ የነበረን (ሰማያዊው እስኪርቢቶ ያጠፋል ያልን)
18. ናና ከረሜላ በ10 ሳንቲም 5 የገዛን እፉዬ ገላ እና አንበጣ ለመያዝ የሮጥን
19 . ሰኔ ሰላሳ ለመደባደብ የጠበቅን
20. ፊኛ ስንገዛ በእጣ ትልቁ እንዲወጣልን የቋጠርን (betting )
21. ስንዝሮ እና Tom & Jerry, jim & jam ትልቁ አኒሜሽን ፊልማችን የነበረ
Jack and the fat man, Mr.Bones,GOD must be crazy, Mr.Been, Apocalipto, Home Alone, Akeelah and the Bee, Titanic ደጋግመን ያየን
የቫንዳም,ስቴቨን ሴጋል,ጄትሊ,ጄኪ ጃን,ሻሩክ,ሸዋሺንገር ከባድ አድናቂዎች የነበርን
22. Nokia 3110 ,Motorola, Sony ericsson የመጀመሪያ ስልካችን የነበረ.......
እናንተ ስንት ቆጠራችሁ?
አስተያየታችሁን ስጡን
541 views19:11