Get Mystery Box with random crypto!

ሰው፣ ጎሬላ፣ ዝንጀሮ ምን ያመሳስላቸዋል? . ምን ያለያያቸዋል? ከት...ከት...ከት...! ብሎ | ድንቃ-ድንቅ

ሰው፣ ጎሬላ፣ ዝንጀሮ ምን ያመሳስላቸዋል? . ምን ያለያያቸዋል?

ከት...ከት...ከት...! ብሎ መሣቅ የሚችል እና ሲስቅም የሚያምርበት ብቸኛ ፍጥረት ሰው ነው፡፥ ስለዚህ ሰው በመሆናችን ከልብ ልንደሰት ይገባል፡፡ አንዳንድ የሚስቁ የእንስሳት አይነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ ጀብ ና ዝንጀሮ ይጠቀሳሉ፡፡ ዳሩ ግን ሲስቁ የተናደዱ እንጂ የተደሰቱ አይመስሉም፡፡

ሳቅ በሽታን የመቋቋም አቅምን ይጨምራል፡፡ ካንሰርን ጨምሮ!!!

ሳቅ የሰው ልጆች ሚስጢራዊ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡

ሲጣሉ እርስ በእርሳቸው የሚሰዳደቡ ፍጥረታት ጎሬላ አና ሰዎች ብቻ ናቸው።

የጎሬላ እና የሰው ልጅ ዘረ መል ወይም ዲ.ኤን.ኤ በ98 ፐርሰንት ደረጃ ይመሳሰላል፡፡

መሳርያ በመጠቀም አደን ላይ የሚሰማሩ ፍጥረታት ሰው እና ቺምፓ'ንዚ ብቻ ናቸው::

እርስ በርስ ቅማል በመቀማመል፣ አንዱ የሌላውን ፀጉር በማበጠር እና አንዱ ሌላውን በመኳኳል በጋራ የሚዋዋቡ ፍጥረታት ሰው፣ ዝንጀሮ እና ቺምፓንዚ ናቸው፡፡

በጀርባው መተኛት የሚችል ብቸኛው ፍጥረት ሰው ነው፡፡ ሰው በጀርባው ተኝቶ ሰርካታ ስራዎችንም መስራት ይችላል፡፡

ራሳቸውን በመስታወት አይተው መልካቸውን መለየት የሚችሉ ፍጥረታት ሰው እና ቺምፓንዚ ብቻ ናቸው፡፡