#ጉጉት - ጉጉት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጥርት አድርጋ ማየት ትችላለች። - ጉጉት አንገትዋን 270 ድግሪ ማዞር ትችላለች። - ጉጉት አይኖቿን በፍጹም ማንቀሳቀስ አትችልም። - ጉጉት ለ እለት ጉርሱ ሌሎች ትናንሽ ወፎችን ከነነፍሳቸው ይውጣል። ከ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ግን ላባቸውን እንደ ኩስ አድበልብሎ ይተፋል ። ጉጉቶች በተጨማሪ አይጦችን፣ አሳዎችን እና ነፍሳቶችን ይመገባሉ - የ ጉጉቶች ክንፍ ለየት ያለ የላባ አቀማመጥ ስላለው የሚያድኑትን እንስሳ ለመያዝ ሲበሩ ክንፋቸው ምንም ድምፅ አያሰማም። - የሰው ልጅ ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ የሚችሉ የጉጉት ዝርያዎች አሉ። ለምሳሌ:- በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ " January 2013" አንድ እስኮትላንዳዊ ወጣት 50 ሴንቲሜትር ርዝመት ባለው ጉጉት ጥቃት ደርሶበት አንድ አይኑን ሊያጣ ችሏል - ዓለማችን ላይ 225 የጉጉት ዝርያዎች አሉ። ትነሹ የ ጉጉት ዝርያ " elf owl" የሚባል ሲሆን ክብደቱ 31 ግራም ቁመቱ ደግሞ 13.5 ሴንቲሜትር ብቻ ነው። ትልቁ የ ጉጉት ዝርያ ደግሞ " eagle owl" የሚባል ሲሆን ክብደቱ 4.2 ኪሎግራም ቁመቱ ደግሞ 190 ሴንቲሜትር ይደርሳል። ምንጭ:- Wikipedia እና የዕውቀት ማህደር 463 views04:58