Get Mystery Box with random crypto!

በህክምና ሙያ ለተሰማራችሁ አማራዎች የቀረበ ጥሪ! እንደሚታወቀው በገዥው ቡድን በተቀመጥንበት በ | Dejen Times

በህክምና ሙያ ለተሰማራችሁ አማራዎች የቀረበ ጥሪ!

እንደሚታወቀው በገዥው ቡድን በተቀመጥንበት በመካናይዝድ ጦር የታገዘ ጦርነት ተከፍቶብናል። ታዋቂ ምሁራኖች፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እና ፋኖዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ በጅምላ ማጎሪያ ቤት ተጥለዋል። ወደፊት ለማሰርም በርካታ ልጆቹ በሽብር እፈልጋቸዋለሁ ብሎ አሰሳ ላይ ነው። የአማራ ባለሃብቶች እና በአማራ ስም የተደራጁ የማህበራት የሂሳብ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። የገነቡት ህንፃም በሀራጅ እንዲሸጥ የገዥው ቡድን የባንክ ተጠሪወች ወስነው የኦሮሞ እና የትግራይ ባለሃብቶች እንዲገዙ ስምሪት ተሰጧቸዋል። በአጠቃላይ አማራነት ወንጀል ሁኖ ጦርነት ተከፍቶበታል።

ስለሆነም ህዝባችንም የታጠቁ ጀግና አርበኞቹን ይዞ የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ስለዚህ በየቦታው ባሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የህክምና አገልግሎት እንድትሰጡ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

የፈራ ይመለስ

ድል ለአማራ!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide