Get Mystery Box with random crypto!

ድል ለአማራ ህዝብ ከአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የተላለፈ የትግል ጥሪ! እንደሚታወቀው የአማራ ህ | Dejen Times

ድል ለአማራ ህዝብ

ከአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የተላለፈ የትግል ጥሪ!

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ላለፍት ሠላሳ እና ከዛ በላይ አመታት በወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ በደል የደረሰበትና ታሪካዊ እርስቶቹን ተነጥቆ የራያና የወልቃይት መተከል ህዝብ የዘር ማፅዳት ተፈፅሞበታ። ሆኖም ግን የአማራ ህዝብ ባደረገው ከፍተኛ ህዝባዊ እምቢተኝነትና ከፍተኛ መስዋዕትነት የወያኔን ስርዓት ታግሎ የጣለ ቢሆንም የወያኔ ልጆች የሆኑት በተራቸው የአማራን ህዝብ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በኦሮምያ፣ በቢኒሻንጉል፣ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ እና አጠቃላይ በኢትዮጵያ በሚባለው ማዕቀፍ ከፍተኛ መንግስታዊ ጭፍጨፋ በዚህ አምስት ዓመት ተፈፅሞበታል።

ነገር ግን ለሀገር አንድነትና ለህዝቦች የጋራ መኖር አብሮነት ሲባል ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ በሚል እሳቢ እየደረሰ ያለውን ግፍ በመቻል ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠል ሲባል አሁን ካለው የብልፅግና መንግስት ጋር በመሆን ወረራ የፈፀመውን የወያኔ ጨካኝ ቡድንን የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚኒሻ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን ሀገርን ከወራሪና ከጠላት መታደግ ተችሏል። በዚህም የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ስቃይና ለከፋ ጉስቁልና ተዳርጓል። በርካቶች በማንነታቸው ተለይተው ተጨፍጭፈዋል: ሀብት ንብረታቸው ወድሟል: ለስደት ተዳርገዋል። ከጭፍጨፋ የተረፉት ደግሞ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ያለ በቂ ምግብ እና መጠጥ በየካሞፖች ይገኛሉ።

ይህ ችግር ስደትና መፈናቀል ሳይሽርና መፍትሔ ሳይዘጋጅለት ዛሬም የትግራይ ወራሪ ኃይል የአማራን ህዝብ ዳግም ለመውረር እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ፤ ትላንት መከላክያን ከመዋረድና ከመፍረስ ያዳነውን የአማራን ህዝብ በብልፅግና መራሹ መንግስት ዳግም ለመግለፅ በሚከብድ መከራና እንግልት እንዲሁም ጦርነት ውስጥ ከቶታል መንግስታዊ ጦርነትም በአማራ ህዝብ ላይ ታውጆበት ወደ ስራ ገብቷል። የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ምክንያት ያጣው ስርዓቱ አቶ ግራማ የሽጥላን በመግደል ላቀደው ኦፕሬሽን እንደምክንያትነት ተጠቅሞበታል።

ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ በሚቀጥሉት ቀናት ከመላው አማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት በሚተላለፍ የትግል ጥሪዎች እራስክን እንድታዘጋጅ እያልን። ከሚያዝያ 28 ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ አድማ በአማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጠርቷል። ስለሆነም መሠረታዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ሆስፒታል ዳቦ ቤትና ክኒሊኮች እንዲሁም አንቡላንስ ውጭ ማንኛውም የንግድ ተቋምና ተሽከርካሪ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

ማሳሰቢያ:- ከተፈቀደላቸው የንግድና አንቡላንሶች ወጭ የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪና የሚከፍት የንግድ ተቋም አስፈላጊውን እርምጃ ይወሰድበታል።

የመላው አማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት!
ነፃነታችን በክንድቻን

ድል ለአማራ ህዝብ

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
ቴሌግራም https://t.me/DejenTimes