Get Mystery Box with random crypto!

በቅድሚያ በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በቅድሚያ በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ መናገሻ ከሆነችው አዲስ አበባ ከተማ 300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘውና የጎጃም ማዕከል በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ስመ ጥር ዩኒቨርሲቲ ነው።

ዩኒቨርሲቲያችን በአሁኑ ስዓት የካበተ የማስተማር ልምድ እና እውቀት ባላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መምህራን በመታገዝ በ63 ትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ድግሪ ፣ በ83 የትምህርት ዘርፎች የ2ኛ ዲግሪ እና 10 በሚሆኑ የትምህርት ዘርፎ ደግሞ በሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል።

ደብረ ማርቆስ ኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ከ54 ሺህ በላይ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን አፍርቶ ለሀገራችን ማህበራዊ ፣ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ ግልጋሎቶች የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ዩኒቨርሲቲያችንን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚለየው በየአመቱ 3.75 እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እውቅና ሽልማት የሚሰጥበት " የተማሪዎች አምባሳዳር " መርሐ ግብር ማዘጋጀቱ ነው። ይህ መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሚበረታቱበት እና ሽልማት የሚሰጡበት ዝግጅት ሲሆን ሌሎቹ ተማሪዎችም በጓደኞቻቸው ውጤት እንዲነሳሱና የውድድር ስሜታቸው እንዲዳብር ዕድል የሚፈጥር መርሐ ግብር ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን ለሶስት ተከታታይ አመታት ይህንን ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ያከበረ ሲሆን ዘንድሮም ለአራተኛ ጊዜ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርቲው የተመሰረተባት የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው አየር ንበረትም ከቆለቀማውም ሆነ ከደጋማው የሀገራችን አካባቢዎች ለሚመጡ ሁሉ ፍፁም ተስማሚ የሆነ ወይና ደጋማ የሚባል የአየር ንብረት ባለቤት ነች፡፡ ማህበረሰቡም ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎችን በመልካም አቀባበል ተቀብሎ የማስተናገድና እንደልጆቹ የመንከባከብ ባህል ያለው ማህበረሰብ ነው፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲያችን ለተማሪዎቹ ምቾት አብዝቶ የሚጨነቅና ፍፁም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ዩኒቨርሲ በመሆኑ ቀዳሚ ምርጫችሁ ብታደርጉት በብዙ እንደምትጠቀሙ እንተማመናለን!!

“የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ”
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የአስተዋዮችና የጎበዞች ምርጫ!

ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫንና በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ

ዌብሳይት www.dmu.edu.et
ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia
እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/