Get Mystery Box with random crypto!

' የቅኝ ግዛት ትርክቶች እና የኢትጵያ ብሔረ መንግስት ግንባታ ቅኝ ባልተገዛችው ኢትዮጵያ ፥ ተረ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

" የቅኝ ግዛት ትርክቶች እና የኢትጵያ ብሔረ መንግስት ግንባታ ቅኝ ባልተገዛችው ኢትዮጵያ ፥ ተረኮች እና እውነታዎች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ትምህረተ -ጉባኤ ተካሄደ።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል " Colonial Narrative and Nation Buliding in a Non-Colonized Ethiopia : Rhetoric Versus Reality " በሚል ርዕስ የደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ምሁራን የተሳተፉበት 25/05/2015 ዓ.ም በንግስተ_ሳባ አዳራሽ ትምህርተ-ጉባኤ አካሂዷል።

በትምህርተ - ጉባዔው መምህር አሳቡ ሰውነት የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ተጠሪ የጉባኤውን የውይይት ፅሁፍ አቅርበዋል።

በፅሑፋቸውም ያካተቷቸው ጭብጦች፦ የሀገረ መንግስት ግንባታ ጽንሰ ሃሳብ፣ የብሔረ መንግሥት ግንባታ ፅንሰ ሃሳብ፣ ቀኝ ግዛት በብሔረ መንግስት ግንባታ ላይ ያሳደረው ተጽኖ እና እውነታዎች ፤ ሀገረ መንግስትና ሉዐላዊነት እንዲሁም ኢትዮጵያ ቀኝ ግዛት አለመገዛቷ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ያመጣው ተጽዕኖ የሚሉ ናቸው።

በሌላ በኩል የቀኝ ግዛት ትርክቶች በሀገረ እና በብሔረ መንግስት ግንባታ ላይ በየዘመኑ በነበሩ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች ላይ የራሱ የሆነ ተጽኖ ማድረጉን ገልፀዋል።

ከጉባዔው ተሳታፊ ምሁራንም ልዩ ልዩ አስያያቶችና ጥያቄዎች የተሰጡ ሲሆን ይህንን ጉባኤ ያዘጋጀውን የፓለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ት/ክፍልም ተመስግኗል።