Get Mystery Box with random crypto!

DBU Daily News

የቴሌግራም ቻናል አርማ dbu11 — DBU Daily News D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dbu11 — DBU Daily News
የሰርጥ አድራሻ: @dbu11
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.82K
የሰርጥ መግለጫ

Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM
👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ
📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል::
Contact @Wende11mekiya

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 22:19:06 መልካም ፈተና ለጤና ተማሪዎች፡ ውጤቱ ምንም ቢሆን ፡ የገነት መግቢያ አይደለም ነገም ሌላ ቀን ነው ፡፡

ተረጋግታችሁ ለመሥራት ሞክሩ ፡፡

ምንም ነገር ከልኩ አያልፍም ፡፡

መልካም ፈተና እንዲሁም ያማረ ውጤት እንዲሆንላችሁ DBU Daily News ይመኝላችኃል ፡፡፡

@DBU11
@DBU111
@DBU_ENTERTAIN
2.6K viewswende Abebe መ'ኪያ, edited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 19:17:56
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ 327 የጤና ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና ያስፈትናል፡፡


ከደብረ ብረሀን ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ከደብረብርሃን ዙሪያና ከአዲስ አበባ ለመጡ ለግል ኮሌጆች የሚመጡ በአጠቃላይ  ለ2057 የጤና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ይፈተናሉ ፡፡

ከጤና ሚንስቴር ፍቃድ ለማደስ የሚፈተኑ ሰራተኞች በዩኒቨርሲቲው እንደሚፈተኑም ተገልፆል ፡፡


መፈተኛ ክፍል ውስጥ ከሰላሳ ደቂቃ
በፊት መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከሰላሳ ደቂቃ በፊት መውጣት እንደማይቻል፣ ከስልክ ጀምሮ ኤሌክትሮኒስ
መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እንደሌለባቸው ተነግሯል ፡፡

የመውጫ ፈተናው ለህክምና ተማሪዎች አዲስ አሰራር አለመሆኑም ተነስቷል፡፡

@DBU11
@DBU11
3.3K viewswende Abebe መ'ኪያ, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 13:02:00 #ኦረንቴሽን

ዛሬ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በዋናው ግቢ የመመረቂያ አዳራሽ ነገ ለሚካሄደው #የጤና ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አጠቃላይ መግለጫ(Orientation) ስለሚኖር የሚመለከታችሁ ተማሪዎች (በግልና በመንግስት የተመደባችሁ) በኦረንቴሽኑ ላይ መገኘት ትችላላችሁ።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
@DBU111
3.6K views【Naty.B】, edited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 18:38:01
ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ከ2200 በላይ ኮምፒውተሮች ለመውጫ ፈተና መዘጋጀቱን አስታወቀ ፡፡

በፈተናው ችግር እንዳይገጥም ከደብረ ብርሃን ከተማ የኤሌክትሪክና የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተቋሞትና ከዩኒቨርሲቲው የተውጣጣ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ በጋራ በፈተናው መሰረተ ልማቶች ዙሪያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም ተገልፆል ፡፡

ዩኒቨርሲቲው እንደ ማእከል ሆኖ የመንግስትና የግል ተቋማት ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 6000 ተፈታኞችን የመውጫ ፈተና እንደሚያስፈትን ተነግሯል ፡፡

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስና በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ 2800 ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይፈተናሉ ብለዋል፡፡

@DBU11
@DBU11
4.1K viewswende Abebe መ'ኪያ, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 13:38:56
በሌቦች አንገቱን ታርዶ በአጋዥ መሳሪያ የሚተነፍሰው ተማሪ

2ኛ አመት ተማሪ እያለ ነበር ትምህርቱን ያቋረጠው።
ጆን ስለሺ ይባላል ትውልድ እና እድገቱ አርሲ ሮቤ ሲሆን ራሱን ሊስትሮ እየሰራ ያስተማረ፤ በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ጥሩ እና ጎበዝ ተማሪ በመሆን ለ2 ዓመት ያህል በትምህርት ገበታው ላይ ቆይቷል። ነገር ግን በአንድ ምሽት በአዳማ ከተማ ከስራው በሚመለስበት ሰዓትብ ጨካኝ  ሰዎች ሊስትሮ ሰርቶ ያገኛትን ገንዘብ ለመንጠቅ ሠላም ነው ብሎ በተሳፈረበት ባጃጅ ላይ አንገቱን ሁለት ቦታ በስለት በመውጋት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበት አንገቱ ውስጥ በገባ ብረት እገዛ ለመተንፈስ ተገዷል::

ይህ ከሆነ 2 ዓመት ሞላው።ግን እንዲህም ሆኖ ሊስትሮ በመስራት ራሱን ችሎ ሊስትሮ እየሰራ ይኖራል።
ለህክምናው ከ1.2 ሚልየን ብር በላይ የሚያስፈልገው ሲሆን እንደ ትምህርት ቤት ወዳጆቹ የተቻለንን እንድንረዳው ድምፅ ልንሆነው ወደናል።

በጨካኞች ሊበላሽ የነበረን ህይወት በመታደግ ዛሬም በሀገራችን ከጨካኞች ይልቅ ደጋጎች እንደሚበዙ እናሳየው። አለን ከጎንህ ነን እንበለው።

ለጆን ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ በስሙ በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000503098605 ላይ ድጋፋችሁን ልትልኩለት ትችላላችሁ።

እሱን ማነጋገር ለምትፈልጉ ደጋግ ሰዎች
በ0931286725
0949379143 ላይ ደውሉለት::

ስለ ቀናነታችሁ ፈጣሪ በበረከት ይሙላችሁ!
4.0K views【Naty.B】, 10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 08:29:15 UPDATE

ባህርዳር፣ደሴ፣ሃዋሳ፣ወላይታሶዶ
እየሞሉ ያሉ የጉዞ መኪኖች ናቸው።የቀረው ቦታ ጥቂት ስለሆነ አስቀድማችሁ ተመዝገቡ።

የ3ቱ ጉዞዎች ሃሙስ የሚደረጉ ሲሆን
ባህርዳር አርብ ሆኗል
4.1K views【Naty.B】, 05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 03:17:09 ከተዘጋጁት ጉዞዎች መካከል ተጓዥ የሞላባቸው የጉዞ ቀናቸው ተወስኖ እስከ እሮብ ማታ የምናሳውቅ ሲሆን ያልተመዘገባችሁ እስከ ውሳኔ ሰዓቱ ድረስ እንድታሳውቁ አናሳስባለን።

ጉዞው ተማሪዎችን ከእንግልት፣በመንገድ ከሚያጋጥም ስርቆት፣ካላስፈላጊ ሸክምና የታክሲ ወጪ የሚታደግ፣ ጊቢ ውስጥ ድረስ ገብቶ በማደር በጊዜ ከመውጣት አንፃር ለተማሪዎች ምቹ ይሆናል


@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
@DBU111
4.1K views【Naty.B】, edited  00:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:23:08 ሃሙስ ደሴ ድረስ 360 ብር በቅጥቅጥ መሄድ የምትፍለጉ ነገ ሮብ ብቻ ምዝገባው የሚካሄድ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ ከላይ የተጠቀሱትን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ።
0961378509
0914988294
0940219376
4.2K views【Naty.B】, edited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:01:13 #ATTENTION
Update ጉዞ
በየትኛውም የጉዞ መስመር ታሪፍ ወጥቶ እንድትመዘገቡ ለቀረበላችሁ ጥሪ እስከ ሮብ ከሰዓት ድረስ ካልተመዘገባችሁ እና ቦታ ካልሞላ ጉዞው ሊቀር ስለሚችል አስቀድማችሁ በመመዝገብ የጉዞ ውሳኔ ቀን እንዲወሰን እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ጉዞው ሃሙስ ወይም አርብ በአብላጫው ፍላጎት የሚሆን ሲሆን
በዋናው ግቢ የሌላችሁ የጤና ተማሪዎች እና NON-Dorm ተማሪዎች በ 0914988294 በመደወል ብር በማስተላለፍ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።


ጉዞ አስተባባሪ
@DBU11
@DBU111
@DBU_ENTERTAIN
4.2K views【Naty.B】, edited  15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:11:29
ALERT
ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።


ትምህርት ሚኒስቴር ከሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።
የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሬሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።
1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ
2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ
3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
@Dbu11
@dbu11
4.5K viewswende Abebe መ'ኪያ, edited  09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ