Get Mystery Box with random crypto!

DBU Daily News

የቴሌግራም ቻናል አርማ dbu11 — DBU Daily News D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dbu11 — DBU Daily News
የሰርጥ አድራሻ: @dbu11
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.82K
የሰርጥ መግለጫ

Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM
👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ
📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል::
Contact @Wende11mekiya

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-20 12:08:07 عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال كل عم وأنتم بخير
ዒድ ሙባረክ
ተቀበል'ላህ ሚና ወሚንኩም
ሷሊሓል አዕማል !!!

መልካም በዓል!
2.8K views【Naty.B】, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 12:05:08 ፊቼ ጄጂ ጨምበላላ

ገንዘብ ያበደረ እንዲመለስለት የማይጠይቅበት፣ ከብት የማይታረድበት፣ ዛፍ የማይቆረጥበት፣ ያጠፉ ይቅር የሚባሉበት ዕለት ነው- ጨምበላላ።

የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ።

በበዓሉ ወቅት ለአካባቢ እና ለእንስሳት ትልቅ ትኩረት ይሰጣል

ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው።


ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። (ባሳለፍነው ዓመት በሚያዚያ 20 ተከብሮ አልፏል) በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል። ከዚያም ለበዓሉ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ይጀመራል።

ከዋዜማው አንስቶ በዓሉ መከበር ይጀምራል። ጎረቤት ተሰብስቦም ከእንሰት የሚዘጋጀውን ቦርሻሜ ተብሎ የሚጠራውን ምግብ በወተት ይመገባሉ።
ያገቡ ሴቶች ልዩ የሆነ የጸጉር አሰራር አላቸው

ለበዓሉ ከሚበሉ ባህላዊ ምግቦችና ከሚከናወኑ ጭፈራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባህላዊ ሁነቶችም ይካሄዳሉ። ቄጠላ፣ ኛፋሮና የመሳሰሉ ሙዚቃዎችም በበዓሉ ይከወናሉ።

ቄጠላ በተባለው ባህላዊ ሙዚቃ፤ አገር፣ ዘመን፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እየተወደሱ ይጨፈራል።
ቄጠላ የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቡድን ሲያዜሙ

''የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው'' የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሃንካራ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ መሆናቸውን ይናገራሉ።

የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

ፊቼ ጨምበላላ ዘንድሮ ያገባች ሴት ሙሽርነቷን ጨርሳ ከሌሎች ሴቶች ጋር የምትቀላቀልበት በዓል ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል።

ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው።

ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል። የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

መልካም በዓል!
@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
@DBU111
2.5K views【Naty.B】, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 12:04:03
2.4K views【Naty.B】, edited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 15:03:48 "የሰው ዋጋው መቼ ይረክሳል?" ቢባል ያለቦታው የገባ ቀን ይባላል።

1 ሊትር ውሃን ከአዟሪ 20 ብር፣ከሱቅ 25 ብር፣ከሱፐር ማርኬት 50 ብር፣ ከሆቴል 100 ብር የመገዛቱ ምስጢር ውሃው 'ውሃነቱ' መጠኑም ጨምሮ ሳይሆን ቦታው የሰጠው ክብር ነው።

ሰው ከዚህም ይበልጣል። ባለንበት ቦታ ልክ እንመዘናለን። ባወቅነው እና በኖርነው ልክ እንከበራለን። በተናገርነው ልክ አስተሳሰባችን ይታወቃል።

እኛ ማን ነን?
በስድብ፣በነቀፋ የተገነባን ስንሆን ዋጋችን ስንት ነው...?
ከብዙ ሰናይ ግብር መልካሙን ላለማየት ስንፈልግ ፣-ve thinkers ስንሆን ዋጋችን ስንት ነው?
አመስጋኝና አበረታች ስንሆን ዋጋችን ስንት ነው?
በምሁራንና በአሻጋሪ ሃሳብ ባላቸው ዘንድ ስንገኝ ዋጋችን ስንት ነው?
በጠንካራ ሰራተኞችና አመፅን ከሚጠሉት ጎን ስንቆም

እኛ ዋጋችን ስንት ነው?
......የሰው ሚዛኑ የተገኘበት ቦታ ነው....

.....ክብር ለሰዳቢዎቻችን...በእናንተ ላይ ተሻግረናል!

ናትናኤል ብርሃኑ
@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
@DBU111
216 views【Naty.B】, 12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 14:03:29 Watch "ኑ እንስቀል|Nu enskel by natnael berhanu በናትናኤል ብርሃኑ" on YouTube


1.6K views【Naty.B】, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:40:03 ወተንስአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ሞትንም በሞቱ አጠፋው፣በመቃብር ሳሉ ሁሉ የዘለዓለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ።

መልካም የትንሳኤ በዓል!
2.7K views【Naty.B】, edited  00:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 09:48:14 https://vm.tiktok.com/ZMYnAQ82a/
3.3K views【Naty.B】, 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 20:06:54

1.8K viewsየአብቃል , 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 11:18:49 ለመላው የክርስትና እምነት ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ መልካም የስቅለት በዓል!

@DBU11
@DBU111
@DBU_ENTERTAIN
2.8K views【Naty.B】, edited  08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:57:26 ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ የጥበብ ቀን እየተከበረ ይገኛል።

ጥበብን ለምታደንቋትም፣ለምትደነቁባትም ተማሪዎች በተለይ ለግቢያችን የኪነጥበብ ቡድን "ሆሄ ተስፋ" መልካም የጥበብ ቀን!

@DBU11
@DBU111
@DBU_ENTERTAIN
2.6K views【Naty.B】, edited  13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ