Get Mystery Box with random crypto!

ረ፡ የማምረቻ ማሽኖችን ከውጪ ሀገር ብቻ ነው መግዛት የሚቻለው? ለደንበኛው የሚገዙ የካፒታል ዕቃዎ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

ረ፡ የማምረቻ ማሽኖችን ከውጪ ሀገር ብቻ ነው መግዛት የሚቻለው?
ለደንበኛው የሚገዙ የካፒታል ዕቃዎች በደንበኛው በራሱ ምርጫ ከሚያቀርበው ድርጅት ነው፡፡ የማሽኖቹ አቅራቢ ድርጅት ከሀገር ውስጥም ከውጪ ሀገርም መሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር የሚገዙት ዕቃዎችን የሚያቀርበው ድርጅት በዓለም አቀፍ መስፈርት በባንኩ ተለክቶ ተመራጭ መሆን መቻሉ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መስፈርት መሰረት ተወዳድሮ እሰካሸነፈ ድረስ የማሽኖች ግዢ ከሀገር ውስጥ አምራችም የፈፀማል፡፡

ሰ፡ ለሚገዛው የካፒታል ዕቃ የኢንሹራንስ ወይም መድን ሽፋን የሚገዛው/ኢንሹራንስ የሚገባው ባንኩ ነው ወይስ ደንበኛው?

የካፒታል ዕቃው ከጉዳትና ከብልሽት እንዲጠበቅ ለማድረግ ደንበኛው ከታወቀ የኢንሹራንስ ኩባንያ በልማት ባንክ ስም በካፒታል ዕቃው ጠቅላላ ዋጋ መጠን አስፈላጊውን ዓይነት የኢንሹራንስ/የመድን ሽፋን የሚገዛ እንዲሁም የተገባው የመድን ሽፋን ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ደንበኛው የሚያሳድስ ይሆናል፡፡

ሸ፡ የካፒታል ዕቃውን ሰርቪስ የማስደረግ/የማስጠገን ሀላፊነት የባንኩ ነው ወይስ የደንበኛው?

የካፒታል ዕቃውን በአግባቡ የመያዝና በአምራቹ ድርጅት በተቀመጠው መደበኛ የሰርቪስ ጊዜ ወቅቱን እየጠበቀ ሰርቪስ የማስደረግ/የማስጠገን ግዴታ የደንበኛው ነው፡፡

ቀ፡ ካሁን ቀደም በባንኩ ፋይናንስ ለተደረጉ ድርጅቶች ተጨማሪ ማስፋፊያ ይሰጣል?

አዎ። እንደአዲስ ባንኩን ለሚቀርቡ የተመሰረቱ ድርጅቶች የማስፋፊያ የማሽን ኪራይ /ብድር/ ለሚጠይቁ  አመልካቾች ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ባንኩ ቀድሞ ፉይናንስ ላደረጋቸው ድርጅቶችም ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት ስኬታማ የስራ እና የፋይናንስ አፈፃፀም ማስመዝገባቸው ሲረጋገጥ ለማስፋፊያ የሚሆኑ የካፒታል እቃዎችን ያቀርባል::