Get Mystery Box with random crypto!

ጠቃሚ መረጃ አይሲቲን መሰረት ላደረጉ ጀማሪዎች እና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የኢኖ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

ጠቃሚ መረጃ አይሲቲን መሰረት ላደረጉ ጀማሪዎች እና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በመተባበር ለፈጠራ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (Innovative SMEs) እና ለጀማሪዎች (Start-ups) ቀጥተኛ ፋይናንስ አቅርቦትን ለማሳደግ ከፊል የብድር ስጋት ዋስትና ፈንድ (Partial Credit Risk Guarantee Fund) ለማቅረብ ፍላጎቱ ላላቸው የቢዝነስ ፕሮፖዛላቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ እነዚህ የፈጠራ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና ጀማሪዎች ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ (Home Grown Economic Reform Agenda) ጋር የሚሄዱ ዘርፎች/ተግባራት ውስጥ ሊተገበር የሚችል የንግድ ሥራ ሀሳብ ያላቸው እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡

ማን ማመልከት ይችላል
• የኢትዮጵያ ዜግነት መታወቂያ ካርድ ያላቸው
• በአይሲቲ ላይ የተመሰረተ ፈጠራ ያለው የንግድ መፍትሄ ያላቸው ጀማሪዎች እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች
• የንግድ ፕሮፖዛላቸውን በድረ-ገጹ ላይ በተሰቀለው ቅርፀት /Format/ መሠረት ለማቅረብ ያዘጋጁ
• ያዘጋጁት የንግድ መፍትሔ በኩባንያ ደረጃ ወይም አስቀድሞ በገበያ ላይ መሆን አለበት።

ስለምልከታው ሂደት፣ የምርጫ ሂደት እና በምርጫው ሂደት ስላሉ መስፈርቶች ለማወቅ ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሰነድ/ምስል ይመልከቱ፡፡

ለዚህ ፕሮግራም ለመመዝገብና ፕሮፖዛላችሁን ለማቅረብ የሚቀጥለውን ሊንክ ተጭነው ይድረሱ
http://registration.mint.gov.et

የማመልከቻ ጊዜ
>ፌብሩዋሪ 30, 2023 ይጀምራል
>ማርች 30 ቀን 2023 ያልቃል

ለተጨማሪ መረጃ፡- 0967-94-45-00 ወይም 0993-53-01-03 ይደውሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዩኤንዲፒ፣ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA)