Get Mystery Box with random crypto!

ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute

የቴሌግራም ቻናል አርማ darulhadis18 — ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
የቴሌግራም ቻናል አርማ darulhadis18 — ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
የሰርጥ አድራሻ: @darulhadis18
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.82K
የሰርጥ መግለጫ

ዳሩል ሀዲስ
የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት
✔ ኢስላማዊ ቤተ መፃህፍት
✔ የቁርአን ሂፍዝ ፕሮግራም
✔ የአረብኛ ቋንቋ እና ሸሪዓዊ ትምህርቶች
معهد دار الحديث لتعليم اللغة العربية والعلوم الشرعية
(أديس أبابا – تأسيس 1436 هے)
«من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين»
👍ዳሩል ሀዲስ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-26 09:55:25 የሁለት ዓለም ስንቅ! በአንድ አገልግል!

ልዩ የመድረክ ፕሮግራም!

ለእህቶች ብቻ!

10ሩን ቀናት እንዴት ለማሳለፍ አቅደሻል?

የትኞቹን?

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር የሆነው ዙልሒጃ አይደል?

አዎ!

እና ታዲያ! አላህ ዘንድ እጅግ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት አይደሉም?

እንዴታ!

ኧረ! እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነዚሁ አስር ቀናት ናቸው።

አሁን ገባኝ!

ታዲያ ከገባሽ እነዚህን አስርት ቀናት እንዴት በአግባቡ ተጠቅመሽ ማሳለፍ እንዳለብሽ ማወቅ አትፈልጊም?

ምን ጥያቄ አለው?

እንግዲያውስ መጪው እሁድ ቀጠሮሽ ከእኛ ጋ ይሁን!

በተጨማሪም

እምነትሽ መዳኛሽን ስብዕናሽን ዘውድሽን የሚዳሰሱ ርዕሶች ።

እሁድ ሰኔ 26፣ 2014
ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

አድራሻ: ፒያሳ የሚገኘው ኸሊፋ ህንጻ አዳራሽ

ለሁለቱም ዓለም የሚጠቅምሽን ስንቅ ይዘሽ ትመለሻለሽ!

ብታረፍጂ ይገርመኛል!

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

@darulhadis18
7.0K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 21:38:45 ሴቶች ለሴቶች ወርሃዊ የሙሃደራ ፕሮግራም

ኑ! ስለ ዋና ካፒታላችንና ስለልጆቻችን በጋራ በመመካከር የተሻለ ማንነት እንፍጠር!

በአላህ ፈቃድ
ዱንያ አኼራ ከኪሳራ ስለሚያድነው እምነታችን

ስለ መልካም የልጆች አስተዳደግ

የምንማማርበትን ድንቅ ፕሮግራም አዘጋጅተን የእናንተን ውድ እህቶቻችንን መምጣት በናፍቆት እየጠበቅን ነው!


ቅዳሜ ሰኔ 11፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:30

አድራሻ

ኢማሙ አህመድ መስጂድ
(አለም ባንክ)


መልእክቱን ሼር እናድርገው።

@darulhadis18
7.4K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 15:56:47
እንኳን ለ1443ኛው ዓ.ሂ የሐጅ ወቅት በሰላም አደረሳችሁ ።

ሐጅ እስልምና ከተገነባባቸው ማእዘናት አምስተኛው ሲሆን አቅሙ የቻለ ሙስሊም በህይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ይህን የአላህን ቤት መጎብኘት የግድ ይለዋል።

እርሶስ አላህ በሰጦት ጊዜና ገንዘብ ይህን የአላህን ቤት ለመጎብኘት ተዘጋጅተዋል?? እንግዲያውስ የነብዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሐጅ አፈፃፀም ስርአት ከጅማሬው እስከ ፍፃሜው ምን እንደሚመስል የምንማርበት ኮርስ ተዘጋጅቶ እርሶን ይጠብቃል።

፦ ጊዜው : ከሰኞ ግንቦት 1- 6 ከዝሁር ሶላት በኋላ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ

፦ አድራሻ : ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ሐጂ አህመድ መህሊ (ስልጤ) መስጂድ

፦ አዘጋጅ ፡ የሐጂ አህመድ መህሊ (ስልጤ) መስጂድ ወጣቶች ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር
2.1K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 00:22:45 አስቸኳይ ጥሪ
በትናንትናው እለት በድንገተኛ ሞት ያጣናት እህታችን ኡስታዛ ነስራ ሙሀመድ ጓደኞች ልጆቿን ለመታደግና ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ከዚህ ቀደም አባታቸው ኡስታዝ አህመድ ሙሀመድ ወደ አኼራ መሄዱ ይታወሳል። የወላጆቻቸውን ውለታ እና የቲምን በመደገፍ የሚገኘውን አጅር በማሰብ በነዚህ ታላላቅ ቀናት ድጋፍ እናድርግ።

በሴቶች ጀመዓ የተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት
1000473088413
Mishkat, Teqiya & Fethiya

___
ተንቢሃት
@tenbihat
1.7K views21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 20:57:12 መርከዛችንን በታህፊዝ አስተማሪነት ለረጅም አመታት ስታገለግል የቆየችው ኡስታዛ ነስራ መሀመድ በኢዕቲካፍ ላይ ሳለች ባጋጣሚ ወደ አኼራ ሄዳለች። አላህ መልካም ስራዋን እንዲቀበላት መጨረሻችንንም እንዲያሳምረው እንለምናለን።

ለቤተሰብዋ፣ ለጓደኞቿ እና ለመላው የመርከዙ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

____
ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት
T.me/darulhadis18
8.4K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 11:41:42 ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

የተለመደው ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

እምነታችን እና

ብዙዎች የተዘናጉባቸው ክልከላዎች
በሚሉ ወሳኝ ርእሶች ትምህርት አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው።

ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ቅዳሜ ሚያዝያ 8፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:00
ቀጠሮአችን በኢማሙ አህመድ መስጂድ ይሁን።

አድራሻ: አለም ባንክ/ አንፎ አል-ጋዚ አደባባይ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!


https://t.me/darulhadis18
8.8K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 14:17:52 እንዳያመልጣችሁ!
ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

የተለመደው የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

ስለተከበረው የእዝነት ወር አቀባበል እና ሌሎች ወሳኝ ርዕሶች ለመተዋወስ

እሁድ መጋቢት 18፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:00
ቀጠሮአችን በኢብኑ መስዑድ ይሁን።

አድራሻ: 18 አደባባይ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!


https://t.me/darulhadis18
10.9K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 09:40:00 ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

የተለመደው ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

የመሰረቶች ሁሉ መሰረት ስለሆነው

አላህን ማወቅ እና

የተከበረውን የእዝነት ...ወርን እንዴት እንቀበለው? እንዴትስ እንጠቀምበት? በሚሉ ርዕሶች ይሆናል።

ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ቅዳሜ መጋቢት 10፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:00
ቀጠሮአችን በኢማሙ አህመድ መስጂድ ይሁን።

አድራሻ: አለም ባንክ/ አንፎ አል-ጋዚ አደባባይ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!


https://t.me/darulhadis18
11.5K viewsedited  06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:08:30 ሂዳያ በነሲሓ የታዳጊዎች የረመዳን ኮርስ || NesihaTv

አስደሳች ዜና ለታዳጊዎች
ኢስላማዊ ዕውቀት መገብየት ትሻላችሁ?
ረመዳንን እንዴት በአግባቡ ልጠቀምበት ብላችሁ ተጨንቃችኋል?
ራሳችሁን መለወጥ ትፈልጋላችሁ?
እንግዲያውስ የብስራት ዜና እነሆ!
ሂዳያ በነሲሓ የረመዳን የታዳጊዎች ኮርስ
ለናንተ በሚመጥን!
ወደችሁ እንድትከታተሉት ሳቢና ማራኪ በሆነ አቀራረብ! የተዘጋጀ "የረመዳን ጉዞዬ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በኮርስ መልኩ ቀርቦላችኋል!

መጽሐፉ እናንተን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን። በውስጡ
ሐዲሦች
ጥያቄዎች
የእቅድ መጻፊያዎች
ራስን መገምገሚያ መጠይቆች እና መመዘኛ ጥያቄዎችን እንዲሁም የምስክር ወረቀት አካቶ ይዟል።

የመጽሐፉ ማብራሪያ ፕሮግራም በነሲሓ ቴሌቪዥን በረመዳን 1433 ይቀርባል።

መጽሐፉን በማንበብ ኮርሱን በመከታተል በረመዳን አዲስ የለውጥ ጎዞ ጀምሩ…
መጽሐፉን ለማግኘት
በአልዐፊያ ትምህርት ቤቶች ሁሉም ቅርንጫፎች
በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ ጣቢያዎች አስራ ስምንት
ቤተል ነሲሓ ቲቪ ቢሮ
አባ ጂፋር (የቀድሞ መርየም) መድረሳ
ቤተል ተቅዋ መስጂድ አካባቢ ባለው መድረሳ
ቃሊቲ ኢሕሳን መድረሳ
ፊሊ ዶሮ አካባቢ ኡማ መድረሳ
አቃቂ ቢላል መስጂድ
በተጨማሪም
ግራር ነሲሓ መድረሳ
አንፎ ኢማሙ ነወዊይ ሒፍዝ ማዕከል
ሎሚ ሜዳ ዐሊ መድረሳ
ስልጤ ሰፈር ሰላም መስጂድ
አብነት 26 ዑመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ እና አልፋሩቅ መድረሳ
ኮካ ቢላል መስጂድ
አንፎ ኢማሙ አሕመድ መስጂድ
ወይራ ሰልማን አላፋሪስ መስጂድ
በክልል ከተሞች
ወሊሶ
ደሴ
ባህርዳር
አዳማ እና
ጉብሬ
እንዲሁም በተለያዩ ኢስላማዊ ማዕከላት ማግኘት ይችላሉ!

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
0930484284
ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር፡፡

@nesihatv
1.8K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ