Get Mystery Box with random crypto!

የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ || NesihaTv ወቅቱ ክረምትና የረፍት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን | ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute

የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ || NesihaTv

ወቅቱ ክረምትና የረፍት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን

ወላጆች ልጆቼ ጊዜያቸውን በምን ያሳልፉ ይሆን? የዲን ትምህርት የት ላስተምራቸው? ብለው የሚጨነቁበት ነው።

ልጆችም በፊናቸው የትና በምን እንደሚያሳልፉ የሚብሰለሰሉበት ወቅት ነው!

እነሆ! ይህን ጭንቀታችሁን የምታቃልሉበት መፍትሄ ይዘን ከተፍ ብለናል!

ክረምቱን የዲን ዕውቀት ስንቅ የምትሰነቁበት ልዩ ገፀ በረከት!

የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ!

በአካል ሄደው መማር ለማይችሉ ዕድሜያቸው ከ8 -13 ላሉ ታዳጊዎች የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ አዲስ የክረምት ኮርሰ በነሲሓ ቲቪ!

ይህ ኮርስ ለታዳጊዎች እንዲሆን ታስቦ ቀለ ባለና ልዩ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለኮርሱ መስጫ አጋዥ መጽሐፍም ተሰናድቷል።

መጽሐፉ በውስጡ የዐቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ ትምህርቶችን ከመመዘኛ ጥያቄዎችን ጋር አካቶ ይዟል።

የመጽሐፉ ማብራሪያ ፕሮግራም በነሲሓ ቴሌቪዥን ይቀርባል።

መጽሐፉን፦

ቤተል ነሲሓ ቲቪ ቢሮ እና

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ማግኘት ትችላላችሁ!

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
09 30 484284

አዘጋጅ፦ ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር!

@nesihatv