Get Mystery Box with random crypto!

የሁለት ዓለም ስንቅ! በአንድ አገልግል! ልዩ የመድረክ ፕሮግራም! ለእህቶች ብቻ! 10ሩን | ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute

የሁለት ዓለም ስንቅ! በአንድ አገልግል!

ልዩ የመድረክ ፕሮግራም!

ለእህቶች ብቻ!

10ሩን ቀናት እንዴት ለማሳለፍ አቅደሻል?

የትኞቹን?

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር የሆነው ዙልሒጃ አይደል?

አዎ!

እና ታዲያ! አላህ ዘንድ እጅግ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት አይደሉም?

እንዴታ!

ኧረ! እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነዚሁ አስር ቀናት ናቸው።

አሁን ገባኝ!

ታዲያ ከገባሽ እነዚህን አስርት ቀናት እንዴት በአግባቡ ተጠቅመሽ ማሳለፍ እንዳለብሽ ማወቅ አትፈልጊም?

ምን ጥያቄ አለው?

እንግዲያውስ መጪው እሁድ ቀጠሮሽ ከእኛ ጋ ይሁን!

በተጨማሪም

እምነትሽ መዳኛሽን ስብዕናሽን ዘውድሽን የሚዳሰሱ ርዕሶች ።

እሁድ ሰኔ 26፣ 2014
ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

አድራሻ: ፒያሳ የሚገኘው ኸሊፋ ህንጻ አዳራሽ

ለሁለቱም ዓለም የሚጠቅምሽን ስንቅ ይዘሽ ትመለሻለሽ!

ብታረፍጂ ይገርመኛል!

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

@darulhadis18