Get Mystery Box with random crypto!

#ሴትየዋና_ጂኒው አንድ ሰው ሚስቱ ጂኒ እንደያዘው ሲያደርጋት 'ጂኒ ሳይዛት አይቀርም' ይልና እን | Hijra Channel🌙

#ሴትየዋና_ጂኒው

አንድ ሰው ሚስቱ ጂኒ እንደያዘው ሲያደርጋት "ጂኒ ሳይዛት አይቀርም" ይልና እንዲቀራባት ወደ አንድ ሸህ ይዟት ይመጣል
ከተቀራባት በኋላ ጂኒው ለመውጣት ዝግጁ እንደሆነና ለመውጣት ግን አንድ መስፈርት እንዳለው ይናገራል
"ካለመስፈርት ነው መውጣት ያለብህ" በማለት ሸይኹ ያስተባብላሉ

ጂኒውም "እስቲ መስፈርቱን ስማኝ"

ሸይኹም "እሺ ተናገር"

ጂኒው "እወጣና ባሏ ውስጥ እገባለሁ"

ባልየው "ይህን ሲሰማ በድንጋጤ ብድግ ይልና
"በፍፁም አይሆንም" ይላል

ጂኒው "ለምን በሱ አካል ልገባ እንደፈለኩ ታቃለህ?"

ሸይኹ "ለምንድነው?"

ጂኒው "ሰላት አይሰግድም"

ሸይኹም ባልየውን "ጂኒው ባለው ትስማማለህ ወይ?" ብሎ ጠየቀው

ባል" ኧረ በፍፁም እንደማይስማማ ተናገረ

ሸይኹም ለጂኒው "ከሴቷ ውጣና ከቤታቸው አቅራቢያ ሁን ሰላት የማይሰግድ ከሆነ ግን ትገባበታለህ" የሚል ሀሳብ አቀረበለት

ጂኒው ተስማማ

ከጊዜያት በኃላ ሴቲቱ ሸይኹን ለማመስገን ደወለች

ሸይኹም ስለባሏ ሁኔታ ጠየቃት

ሚስትም "የመስጂድ በር የሚከፍተው እሱ ነው፡፡ አንዲት ሰላት አምልጣው አታቅም" አለች

የሚገርመው ሚስት ሲጀምርም ጂኒ አልያዛትም ነበረ ቧሏ ሰላት ስለማይሰግድ ጂኒ እንደያዘው ሰው መስላ ቧሏ ሰጋጅ እንዲሆን ከሸይኹ ጋ ተነጋግረው የፈጠሩት ዘዴ ነበረ
በዱንያም በአኺራም ለባሏ ቅጣትን የምትፈራለት ባሏን ከልቧ የምትወድ ምርጥ ሴት ማለት ይህች ሴት ናት

@Damemaka
@Damemaka