Get Mystery Box with random crypto!

መከራና ችግር ለምን እንጠላለን?? ደስታ ከመከራ ውስጥ ይወለዳል። የተኮረኮመ በድሎት ካደገ | Hijra Channel🌙

መከራና ችግር ለምን እንጠላለን??


ደስታ ከመከራ ውስጥ ይወለዳል።
የተኮረኮመ በድሎት ካደገው በላይ ጥንካሬ ይኖረዋል።

ህፃን ልጅ በመቆም የሚፀናው ብዙ ወድቆ ከተነሳ ቦኋላ ነው።

ተርበው የበሉት ምግብ ይጣፍጣል።

ተጠምተው የጠጡት ውሃ ይጥማል።
ላብን አንጠፍጥፈው ያገኙት ገንዘብ ያረካል።
ወድቀው ተነስተው ተቸግረው ያገኙት ነገር በረከት አለው።
ችግርን በመጥፎ ጎኑ ብቻ አናስብ።
የጨለማ ጥቁረቱ ብቻ አንመልከት።
አላህ እንዲህ ይላል
ከችግር ቦኋላ በእርግጥ ምቾት አለ።

Share & join

@Damemaka
@Damemaka