Get Mystery Box with random crypto!

አኺራችንን እናስቀድም ~ * ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ | Hijra Channel🌙

አኺራችንን እናስቀድም
~
* ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።
* ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።
* ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።

~ ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው እራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም። አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ። አላህ ነፍስያችንን ረግጠን ለትእዛዙ የምናድር ያድርገን

IbnuMunewor