Get Mystery Box with random crypto!

ማህበረ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

የቴሌግራም ቻናል አርማ cwwwa — ማህበረ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ
የቴሌግራም ቻናል አርማ cwwwa — ማህበረ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ
የሰርጥ አድራሻ: @cwwwa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 364
የሰርጥ መግለጫ

ይህ #ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ማህበር ነው
መዝሙር ጥናት
የ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት
እግዚአብሔርን አክብረው እሱም ላከበራቸው ቅዱሳን ቀናቸውን እና ዜና ገደላቸውን(1-30) የምናይበት
የ ተቸገሩ እህት ወንድሞች መረዳት
ነዲያንን ማልበስ ና ማብላት
ቤተ-ክርስቲያን የሌላቸውን ቅዱስ ነገሮች ማሟላትና ማገዝ
እግዚአብሔር በፈቀደው መጠን እንሠራለን

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-19 21:29:07 ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።

ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እንደጻፉት)
49 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 10:12:13 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለካው
ክፍል ሁለት
Size:- 19.6MB
Length:-1:25:44

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
84 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 10:11:17 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለካው
ክፍል አንድ
Size:- 14.5MB
Length:-1:33:03
70 views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 22:03:59 ሐድስ መዋዕሊነ ከመ ትካት

      ትርጉም

አቤቱ ዘመናችን እንደቀድሞው አድስ
    ሰቆ.ኤር ም ፭ ቁ ፳፩
                    5     21

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በስላም አሻጋግረን

፳፻፲፭ ዓ.ም

እንኳን ለርዕስ ዓውደ ዓመት ለሊቀ መላዕክት መጋቤ ብርሃናት ቅዱስ ራጉኤል በዓለ ለቅዱስ ኢዮብ ለቅዱስ በርተሎሜዎስ ለቅዱስ ሚልኪ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ መለኮት  በዓል በስላም በጤና አደረሳችሁ አደረስን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

መስከረም ፩ (1)ወርዕስ ዓውደ ዓመት ኢዮብ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት ሚልኪ ወበርተሎሜዎስ

ዘነግህ ምስባክ

ወትባረክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
ወይረውዩ አድባረ በድው

ትርጉም

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ
ጫካውም ስብን ይጠግባል
የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ

     መዝ ፷፬-፲፩
            64   11

ወንጌል

ሉቃ ም ፬ ቁ ፲፮-፳፫
          4     16  23

የቅዳሴ ምንባባት

፪ ቆሮ ም ፮ ቁ ፩-፲፩
ያዕቆብ ም ፭ ቁ ፰-፲፫
ግብ.ሐዋ ም ፭ ቁ ፲፪-፲፯

ምስባክ

አድኀነኒ እምአለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ
ወአውጽኣ እምቅሕ ለነፋስየ
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ

ትርጉም

አቤቱ ስምህን አመሰግን ዘንድ
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት
ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ

     መዝ ፻፵፩-፮
            141   6

  ወንጌል 

ማቴ ም ፲፩ ቁ ፩-፳
           11    1   20

  ቅዳሴ 

ዘወልደ ነጎድጓድ አው ሐዋርያት

" በጨለማ በነበሩ አሕዛብ ውስጥ ነጋሪት ጩኸው መውለድህን ስላስተማሩ ስለ ቅዱሳን ነቢያትም ሁሉ ብለን "
   ቅዳሴ ዮሐንስ ዘወልደ ነጎድጓድ
         ም ፩ ቁ ፶፫
             1     53

  ዘመኑን ዘመነ ብርሃን ዘመነ ሐሴት ዘመነ ፍስሐ ያድርግልን የተባረከ ዘመን ይሁንልን ቸሩ መድኃኔዓለም ዘመን በፀጋ የሚቀይር ዘላለም ሥላሴ ሁላችንም ለንስሐ ህይወት ያብቃን በቸርነቱ ይማረን ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ ማርያም ዘመኑን ትባረክልን ከሊቀ መላዕኩ ከመጋቤ ብርሃናት ቅዱስ ራጉኤል በምልጃው ይጠብቅን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከቅዱሳን ሐዋርያት በረከታቸው ይደርብን በዓሉ በዓለ ምህረት በዓል ድኀነት ያድርግልን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱሳን ይሰውረን ጸሎተ ሙሴ ወምናሴ ዕጣነ አሮን ወዘካርያስ ቅዳሴ መላዕክት የተቀበለ አምላክ ቅዱስ ኢዮብ የኛም ፀሎት ምሥጋና ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለቅዱስ ኢዮብ ፅናት ትዕግሥት የሰጠ አምላክ ለኛም የእምነት ፅናት ለሁላችን ያድለን ነፍሳት ሙታን ይማረን ሕያዋን ይጠብቅልን ለብርሃነ መስቀሉ በስላም ያድርሰን ከአባታችን ከቅዱስ ኖኀ በረከቱ ይደርብን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ክህነት ያላችሁ አምላክ ዓቢየ እግዚእ አምላክ መልከጼዴቅ ክህነታችሁ ይባረክላችሁ ወጣቶች ደግሞ አምላክ መርቆሬዎስ ወጣትነታቸውን ይጠብቅላችሁ የተባረከ ዘመን ዘመነ ሉቃስ ያድርግልን ለቤተክርስቲያን ቅድስት ስላሟ ያብዛልን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቸርነቱ ይጠብቅልን

     https://t.me/cwwwa
110 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:34:32
ጳጉሜን ፪፦

ሰላም እብል ለብእሲ ኃዳፍ፤
በደኃሪ ሐዋርያ ወበቀዳሚ ፍልሱፍ፤
ቲቶ ከዊኖ ረድአ ክርስቶስ ለዘልፍ፤
ምስለ ጳውሎስ ወዮሐንስ በከመ ይቤ መጽሐፍ፤
በንጽሕ ወበትህትና ወበምግባር ትሩፍ!
111 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:32:29 ††† እንኳን ለቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ †††

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው አሥራ አራት መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኳ ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::

ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?
ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ ውስጥ: ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ ከእሥራኤልም: ከጽርእም (ግሪክ ለማለት ነው::) ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን ነበር::

መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::

ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ: ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራዕይ ተገለጠለት::

በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው::" ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ:: የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም::

ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው::" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::

"ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው::" አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::

እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ::" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ::" ብሎ ላከው::

ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ:: ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::
1.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ: አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ::
2.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ ዘላለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል::" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::

በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ደመረው:: የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ: በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል:: ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አስተምሯል::

ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኳቸውም በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን::

††† ጳጉሜን 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)

††† ወርኀዊ በዓላት
(የለም)

††† "የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ. . . መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ: ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ: በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ለሚሆን ልጄ ቲቶ::
ከእግዚአብሔርም አብ: ከመድኃኒታችንም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን::" †††
(ቲቶ. ፩፥፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
96 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 10:24:35 ወደ እግዚአብሔር መገስገስ

"የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው

የተደበቁ ነገሮችን መሰርሰር ትፈልጋለህ ፣ በአደባባይ የተሰቀለውን ጌታ ለማየት ግን ዓይንህን ትጨፍናለህ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቋንጣ የሚሆነውን ዜና ተሻምተህ ትሰማለህ የዘላለሙን ምሥጢር ግን ችላ ትላለህ ፡፡ የመድኃኒት ሰዓትህን ለማስታወስ ማንቂያ ደወል ትሞላለህ ፣ ቅዳሴ ለመሄድ ግን ሲቀሰቅሱህ ትቆጣለህ ፡፡ የኤምባሲ ቀጠሮህን አትረሳም ፣ ሞትን ረስተህ ግን እንዳሻህ ትናገራለህ

ጦም መቼ ይያዛል የሚለውን ታውቃለህ ፣ ለምን እንደሚጦም ግን አትጠይቅም ፡፡ ፋሲካ መቼ ነው ? ብለህ በግ ትገዛለህ ፣ የታረደውን በግ ክርስቶስን ግን ገሸሽ ትላለህ ፡፡ ዘመን ሲለወጥ እንኳን አደረሳችሁ ትላለህ ያደረሰህን አምላክ ግን ከልብ አታመሰግንም ፡፡ ዘመን ሲጨመርልህ ከመለወጥ ያልጨረስከውን ክፋት ለመፈጸም እንደ ገና ታስባለህ፡፡ እባክህን አንተ ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ልዑሉንም ማስተዋል ጥበብ ነው ፡፡ እርሱን ስታውቅ በማይናወጠው መንግሥቱ ያሳርፍሃል ፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ያጸናሃል

 
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲                      ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
151 views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:23:18
141 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:23:06 6፤14-15 ይህ በመሆኑ ስለሰላም ሲባል ይቅር መባባል ለራስም ከእግዚአብሔር ይቅርታን ያስገኝልናል፡፡ ከሰዎች ጋር ኅብረት አንድነት ሰላም ሲኖረን ስለ ሰላም ስንል ይቅር የምንል ከሆነ እግዚአብሔር እኛም የሠራነውን ኃጢአት ይቅር ይለናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰላም ትልቅ ሀብት ስለሆነ ነው ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ (ሮሜ.12፣18) በማለት አስተምሯል፡፡

2) ሰላም አምላክን የምናይበት መነጽር ነው (ዕብ.12፣14)፡፡ ቅዱስ ዳዊት ሕግህ ለመንገዴ ብርሃን ነው እንዳለ ከእግዚአብሔር ጋር ከሆንን ሰላም አለን፡፡ ሰላም ካለን ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ይኖረናል፡፡
3) ሰላም ከእግዚአብሔር ብጽዕናን ያሰጣል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ ብጹዓን ትምህርቱ ሰላምን የሚመሠርቱ ዕርቅን የሚያደርጉ ብጹዓን ናቸው (ማቴ 5፡9) በማለት ሰላም ወደ ብጽዕና የሚያደርስ መሆኑን አስተምሯል፡፡ በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያን በሕዝቧ መካከል ሰላምን የመመስረት ሥልጣን ስላላት ሰላም እንዲመጣ በመጸለይና ሀብተ ክህነት በሰጠቻቸው ካህናት አማካኝነት ለልጆቿ ብሎም ለዓለሙ ሁሉ የሰላም መልእክት እንዲደርስ ታደርጋለች፡፡
4) ሰላም ግጭትን የማስወገጃ መሣሪያ ነው፡፡ ዕርቅና ሰላም ግጭትን የማቆም ታላቅ መሣሪያ ነው፡፡ በጥበብ በደግነት የተነገረች ምላስ /ንግግር/ ቁጣን ታበርዳለች እንዳለ ጠቢቡ፡፡ የአንድ ቀን ጽንስ፣ የአንድ ቀን ልደት የነበራቸው ያዕቆብና ዔሳው በመካከላቸው የነበረው ጠብና አሳዳጅነት መፍትሔ ያገኘው በሰላም ነው (ዘፍ27፡41-46) ። ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም ሰላምን ትቶ ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ይገኛል (ዮሐ 2፡11) እንዳለው የጨለማን መንገድ ትቶ ወደ ብርሃን መንገድ ወደ ሰላም መመለስ ያስፈልጋል፡፡
ሰላም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ክፋት ደግሞ ከዲያብሎስ የመጣ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጸጋ ጠብቀን የዲያብሎስን ሸንገላ ተቋቁመን በዚች አጭር ዘመናችን ከታመንን በምድር ሳለን የእግዚአብሔር ሰላም አይለየንም፡፡በምድር ዕድሜያችን ይረዝማል በሰማይም መኖሪያ ይዘጋጅልናል፡፡ ስለ ሰላም ተረድተን በጥንቃቄ ከኖርን የሰላም አምላክ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡ ስለሀገር፣ ስለሃይማኖት፣ ስለማኅበረሰብ ስለ ግለሰብ ሰላምም እንጨነቃለን፡፡ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ ደህና ሁኑ ፍጹማን ሁኑ ምክሬን ስሙ በአንድ ልብ ሁኑ በሰላም ኑሩ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል (1ቆሮ፡1-2)

ተው ተው አይበጀንም

ተው በሉልኝማ ይሄን ሰው ከሰማ

ይወርድ ከሆነ ከእብሪቱ ማማ

ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል
ቀበሮ ና ተኩላም ይራኮትበታል

ይሄን ሰው ተው በሉት እንዳይጎዱብን
በእኛ ተደግፈዉ ሚጮሁት ኋላችን

https://t.me/cwwwa
125 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:23:06 ሰላምን እሻ ተከተላትም( መዝ 33:14)

ሰላም የሚለው ቃል ሰለመ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የአእምሮ እረፍት፣ መግባባት፣ ውይይት፣ መመካከር ፣ የተረጋጋ ሁኔታ ያለበት ሲሆን ቅሬታ፣ ረብሻ፣ ሁከት ጦርነት የሌለበት ነው፡፡ ሰላም አንድ ሰው ሳይጨነቅ፤ ሳይታመም፤ ሳያዝን፤ በግሉም ሆነ ከሰዎች ጋር ስምምነት መኖርን ያመለክታል፡፡ ሰላም በንግግር፤ በአካላዊ እንቅስቃሴ ይገለጻል፡፡ ሰላም የተቀደሰ ከመሆኑ የተነሳ ቅዱስ ጳውሎስ በተቀደሰው አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ እያለ ያስተምረናል፡፡ ሮሜ 16፤16፡፡

ሀ) እውነተኛ ሰላም ከእግዚአብሔር ነው

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰላም ቅዱስና ከእርሱ የሚሰጥ መሆኑን እንዲህ ብሎ አስተምሯል፡፡ ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፡፡ (ዮሐ. 14፤ 27)

በዚህ መሠረት ሰላምን የመሰረተ፤ ሰላምንም የሚሰጥ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ፡-
ሰላም ክርስቶስ ነው( 2ተሰ.3፤16) በመሆኑም በእሱ ያለንን እምነት በማጠንከር (ዮሐ.16፤33) አድርጉ ያለውንም በተግባር በመሥራት (1ኛ ጴጥ.12፤18) ሰላምን መጠበቅ ይገባል፡፡ አታድርጉ ያላቸውን አለማድረግ ይገባል፡፡ ኢሳይያስ በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ፡፡ ኢሳ. 26፤3 እንዳለ ሰላማችን ክርስቶስን አምነን በትዕዛዙ መኖር ይገባል፡፡
ሰላም ክርስቶስን መምሰል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተ እኔን ምሰሉ ብሎ አስተምሮናል፡፡ ክርስቶስ አብነታችን ነውና ክርስቲያን የሆንን ሁሉ ሰላምን ገንዘብ ልናደርግ ይገባል፡፡ በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ሊይዘው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም ሰላምን የሚመሰርቱ እርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡፡ ማቴ.5፤9 ብሏልና አምላካችን፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቅድስና በንጽሕና መኖር ይገባል ( ሮሜ. 15፤13፡ 1ቆሮ.14፤33)፡፡
ሰላም የክርስቶስ ስጦታ ነው፡፡ በደሙ ያወጀልን ስጦታ ነው፡፡ ቆላ.1፤19 የሰላም ጠላት ዲያብሎስ ክፋትን፤ ተንኮልን ፈጥሯል ዘፍ.3፤1 በዲያብሎስ አማካኝነት የተፈጠረው ክፋትና ተንኮል እንዲጠፋ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም መጥቷል፡፡ ሰላምንም መልሷል፡፡ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፡፡ እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡(ቆላ 1፡19-20)። መጠበቅ ስለ ሰላም መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሰላም ጠላቱ ዲያብሎስ በመሆኑ የሰው ልጆችም ጠላት ዲያቢሎስ በመሆኑ በዲያቢሎስ ተንኮል እንዳንወድቅ ሰላምን በእንክብካቤ መያዝና ሰላምን መጠበቅ ይገባል፡፡ ዲያቢሎስ ሰላም ስለሚያስጨንቀው ሰላምን ለማጥፋት ዘወትር ይተጋልና፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ስጦታ ልንጠብቅ ልንከባከብ ይገባል፡፡

ለ) ሰላም ስለሌሎች በማሰብና ለኛ የሚገባውን ለሌሎች በማደረግ ትጠበቃለች፡፡

አብርሃም አባታችን ሰላምን ይንከባከባት ነበር፡፡ አብርሃም ከሎጥ ጋር የነበረው ፍቅር እንዳይቀዘቅዝ፣ ሰላምንም እንዳያጣ ሰላምን ተንከባክቦ የዲያቢሎስንም ተንኮል በጥበብ አሸንፏል፡(ዘፍ 13፡5)። በእኔና በአንተ መካከል ጠብ መነሣት የመለያየትና የመራራቅ መንፈስ መኖር የለበትም፡፡ እኛ ወንደማማቾች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ፡፡ ወንድሜ ሆይ ምድር በፊትህ አይደለችምን አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፡፡ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ግራውን እወስዳለሁ በማለት በምድር ከሚገኘው ሀብት፣ ንብረት፣ብዕል በላይ ከወንድም ጋር ሰላም መሆን እንደሚበልጥ አውቆ ሰላምን ጠበቃት፡፡ ያውም ሰው ሳይበዛ የምድር ሀብትም ሳይነካ፡፡

ሐ) ሰላም የመንፈሰና የጽድቅ ፍሬ ተብሎ የተገለጸ ነው፡፡ ይህን ፍሬ ያላቸው ሰዎች ለጽድቅ የሚበቁ መሆኑን ተገልጾ በዲያብሎስ የተፈጠረው ተቃራኒው ፀብ፣ ጥላቻ፣ ክፋት ደግሞ የሥጋ ሥራ ተብለው ተገልጸዋል፡፡ ፀብን፣ጥላቻን፣ክርክርን የሚያደርጉ መንግሥተ ሰማይ እንደማይገቡ ይገልጻል (ገላ 5፡19-22)።
እንደ ልቤ ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠውና ገና በልጅነቱ በሰላም ተረጋግርቶ መኖር እና በክፉዎች ምክንያት ደግሞ ሰላምን አጥቶ መንከራተት የተፈራረቁበት ቅዱስ ዳዊት ስለ ሰላም ሲናገር ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፡፡ ሰላምንም እሻ መዝ34፡14 ሲል የሰላምን ጥቅም የክፋትን ጐጂነት አስረድቷል፡፡
ሰላም ሲኖር የሰው ልጅ እድሜው በምድር ይረዝማል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረትም ይኖረዋል፡፡ ሰላም በጋራ ለምንኖርባት ዓለም ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ሰላም ከሌለና ክፋት ከነገሠ፤ ሰው መረጋጋት አይችልም፡፡ ተኝቶ እረፍት አያገኝም፡፡ ሠርቶ አይረካም፡፡ እድሜውም ያጥራል፡፡ ሰዎች የእርስ በእርስ ሰላም ከሌላቸው አንዱ አንዱን ይቀማል፡፡ አንዱ አንዱን ይገድላል፡ የቃየልን ግብር ይፈጸማል፡፡ ጦርነት፣ ስደት፣ ይቀጥላል፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት የክፋት ውጤቱ በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማኅበረሰብ፣ በሀገር፣ በዓለም ለይ የሚያስከትለውን ጉዳት በዘመኑ ተረድቶ፣ በትንቢት መነጽር ተረድቶ ሰላምን እሹ ፈልጓትም ያለው፡፡
በጥንተ ተፈጥሮ ተሰጥታን የነበረችውን ሰላም፡፡ አዳም አባታችን በዲያብሎስ ሲቀማ ሰላምን ለመመለስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ ሰላም አጥተውና ተለያይተው የነበሩት ስውና መላእክት ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፡፡ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ (ሉቃ2፣14) እያሉ የሰላምን መመለስ አብስረዋል፡፡ ሰላም ቅዱስ ስለሆነ ይዘመርለታል፡፡

ጌታችን ሐዋርያትን የሰላምንና የወንጌልን መልእክት ይዘው ለዓለም እንዲያበስሩ ሲልካቸው ወደምትገቡበት ሀገር ሁሉ አስቀድማችሁ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ፡፡ በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል (ሉቃ 10፡5-6) በማለት የእግዚአብሔር ሰላም ለሰው ልጆች አስፈላጊና ለሚፈልጉትና ለሚጠቀሙበት የሚበዛ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ነህምያ ከሀገሩ ኢየሩሳሌም ተማርኮ ወደ ሱሳ ተሰዶ ሳለ ሰላም አጥቶ ይጨነቅ ነበር፡፡ የኅሊና እረፍትም ማግኘትም አልቻለም፡፡ የሀገሩ ናፍቆትና የሀገሩ ፍቅር ሰላም ማጣት አስጨንቆት ሲኖር ሳይማረኩ የነበሩ የይሁዳ ሰዎች እሱ ወዳለበት ሲመጡ ኢየሩሳሌም እንዴት ናት? ብሎ ጠየቃቸው የተጠየቁት ከምርኮ የተረፉት እስራኤላዊያን ኢየሩሳሌም ቅጥሯ ፈርሷል፡፡ ሕዝቡም በመከራ ላይ ነው ብለው ነገሩት፡፡ነህምያ አለቀሰ መፍትሔው ሰላምን ወደሚሰጠው አምላክ ማልቀስ ማዘን ነውና ለአምላኩ ሐዘኑን በለቅሶ ነገረ፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶት የተማረከበት ሀገር ንጉሥ ኢየሩሳሌምን እንዲሠራ ፈቅዶለት የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሠርቷል፡፡ ሕዝቡንም አጽናንቷል፡፡ ሰላምንም አግኝቷል፡፡ ነህ 2፡1-8 ስለዚህ ለምንጊዜም ቢሆን በሀገር በሕዝብ መሐከል ሰላም ሲጠፋ የሰላም ምንጭ የሆነው እግዚአብሔርን መማጸን ተገቢ መሆኑን ያስረዳል፡፡

የሰላም ጥቅም
_____
1) ሰላም ከእግዚአብሔር ይቅርታ የምናገኝበት ነው፡፡ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ያላችኋል፡፡ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማይ አባታችሁ ይቅር አይላችሁም፡፡ ማቴ.
103 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ