Get Mystery Box with random crypto!

6፤14-15 ይህ በመሆኑ ስለሰላም ሲባል ይቅር መባባል ለራስም ከእግዚአብሔር ይቅርታን ያስገኝልናል | ማህበረ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

6፤14-15 ይህ በመሆኑ ስለሰላም ሲባል ይቅር መባባል ለራስም ከእግዚአብሔር ይቅርታን ያስገኝልናል፡፡ ከሰዎች ጋር ኅብረት አንድነት ሰላም ሲኖረን ስለ ሰላም ስንል ይቅር የምንል ከሆነ እግዚአብሔር እኛም የሠራነውን ኃጢአት ይቅር ይለናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰላም ትልቅ ሀብት ስለሆነ ነው ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ (ሮሜ.12፣18) በማለት አስተምሯል፡፡

2) ሰላም አምላክን የምናይበት መነጽር ነው (ዕብ.12፣14)፡፡ ቅዱስ ዳዊት ሕግህ ለመንገዴ ብርሃን ነው እንዳለ ከእግዚአብሔር ጋር ከሆንን ሰላም አለን፡፡ ሰላም ካለን ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ይኖረናል፡፡
3) ሰላም ከእግዚአብሔር ብጽዕናን ያሰጣል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ ብጹዓን ትምህርቱ ሰላምን የሚመሠርቱ ዕርቅን የሚያደርጉ ብጹዓን ናቸው (ማቴ 5፡9) በማለት ሰላም ወደ ብጽዕና የሚያደርስ መሆኑን አስተምሯል፡፡ በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያን በሕዝቧ መካከል ሰላምን የመመስረት ሥልጣን ስላላት ሰላም እንዲመጣ በመጸለይና ሀብተ ክህነት በሰጠቻቸው ካህናት አማካኝነት ለልጆቿ ብሎም ለዓለሙ ሁሉ የሰላም መልእክት እንዲደርስ ታደርጋለች፡፡
4) ሰላም ግጭትን የማስወገጃ መሣሪያ ነው፡፡ ዕርቅና ሰላም ግጭትን የማቆም ታላቅ መሣሪያ ነው፡፡ በጥበብ በደግነት የተነገረች ምላስ /ንግግር/ ቁጣን ታበርዳለች እንዳለ ጠቢቡ፡፡ የአንድ ቀን ጽንስ፣ የአንድ ቀን ልደት የነበራቸው ያዕቆብና ዔሳው በመካከላቸው የነበረው ጠብና አሳዳጅነት መፍትሔ ያገኘው በሰላም ነው (ዘፍ27፡41-46) ። ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም ሰላምን ትቶ ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ይገኛል (ዮሐ 2፡11) እንዳለው የጨለማን መንገድ ትቶ ወደ ብርሃን መንገድ ወደ ሰላም መመለስ ያስፈልጋል፡፡
ሰላም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ክፋት ደግሞ ከዲያብሎስ የመጣ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጸጋ ጠብቀን የዲያብሎስን ሸንገላ ተቋቁመን በዚች አጭር ዘመናችን ከታመንን በምድር ሳለን የእግዚአብሔር ሰላም አይለየንም፡፡በምድር ዕድሜያችን ይረዝማል በሰማይም መኖሪያ ይዘጋጅልናል፡፡ ስለ ሰላም ተረድተን በጥንቃቄ ከኖርን የሰላም አምላክ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡ ስለሀገር፣ ስለሃይማኖት፣ ስለማኅበረሰብ ስለ ግለሰብ ሰላምም እንጨነቃለን፡፡ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ ደህና ሁኑ ፍጹማን ሁኑ ምክሬን ስሙ በአንድ ልብ ሁኑ በሰላም ኑሩ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል (1ቆሮ፡1-2)

ተው ተው አይበጀንም

ተው በሉልኝማ ይሄን ሰው ከሰማ

ይወርድ ከሆነ ከእብሪቱ ማማ

ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል
ቀበሮ ና ተኩላም ይራኮትበታል

ይሄን ሰው ተው በሉት እንዳይጎዱብን
በእኛ ተደግፈዉ ሚጮሁት ኋላችን

https://t.me/cwwwa