Get Mystery Box with random crypto!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን በላይ ሆነ *********** | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን በላይ ሆነ
**************************

ከትናንት እሑድ ዕለት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊየን በላይ መሆኑን የሮይተርስ መረጃ አመለከተ።

ባለፉት 30 ቀናት የታየው ሁለተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሩብ ያህሉን አስተዋጽኦ ማድረጉን መረጃው አትቷል።

ያሳለፍነው ጥቅምት ወር ወረርሽኙ እጅግ የከፋበት ጊዜ የነበረ ሲሆን፣ አሜሪካ በየቀኑ ከ100 ሺህ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባት ሀገር ሆናለች።

በተመሳሳይ አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዘው ሰው ቁጥር መጨመር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለታየው ታማሚዎች ቁጥር ማሻቀብ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ባለፉት ሰባት ቀናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአማካይ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ540 ሺህ በላይ መድረሱንም ዘገባው አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት ከቻይና በተነሣው በዚህ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ከአንድ ነጥብ 25 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።

ወረርሽኙ በቅርቡ ያሳየው ፍጥነት ከባድ ሲሆን፣ ከ30 ሚሊየን ወደ 40 ሚሊየን ለመሻገር የወሰደበት ጊዜ 32 ቀናት ብቻ ነው።

ከዚያም 10 ሚሊየን ተጨማሪ ታማሚዎች ለመድረስ ደግሞ 21 ቀናት ብቻ ጠይቋል ተብሏል።

@coronainethiopia