Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 364 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 607 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ****** | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 364 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 607 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

***************

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 628 የላቦራቶሪ ምርመራ 364 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 93 ሺህ 707 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 607 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 48 ሺህ 150 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 437 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 118 ሰዎች መካከል 314 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 449 ሺህ 170 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@coronainethiopia