Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 629 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 724 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ****** | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 629 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 724 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

***************

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 454 የላቦራቶሪ ምርመራ 629 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 92 ሺህ 858 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 724 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 46 ሺህ 842 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 419 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 595 ሰዎች መካከል 306 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 437 ሺህ 497 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል

@coronainethiopia