Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 630 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 489 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 630 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 489 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 602 የላቦራቶሪ ምርመራ 630 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 90 ሺህ 490 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 489 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 43 ሺህ 638 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 371 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 45 ሺህ 479 ሰዎች መካከል 301 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 410 ሺህ 496 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።


@coronainethiopia