Get Mystery Box with random crypto!

ኮሮና ቫይረስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ፣ የስልክ ስክሪኖች ላይ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ለ28 ቀናት | Coronavirus in Ethiopia & The rest

ኮሮና ቫይረስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ፣ የስልክ ስክሪኖች ላይ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ለ28 ቀናት ሳይሞት ቆይቶ በሽታ ሊያስተላለፍ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

የአውስትራሊያ ብሔራዊ ሳይንስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ጥናት ሳርስ-ኮቭ-2 የሚል ሳይሳዊ መጠሪያ ያለው ኮሮናቫይረስ ከተገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ በቁሶች ላይ እንደሚኖር ያረጋገጠ ነው።

ኮሮናቫይረስ በብዛት የሚተላለፈው ሰዎች ሲያስሉ ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲነጋገሩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ አዲሱ የተመራማሪዎች ግኝት ቫይረሱ ከቁሶች ወደ ሰዎች የሚተላለፍበት መጠንም ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ምንጭ፦ BBC

@coronainethiopia