Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 4 ሺህ 951 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ55 ሰዎች ህይወት ደ | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 4 ሺህ 951 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ55 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል
************

በኢትዮጵያ ከሰኞ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ስድስት ቀናት ብቻ በተደረገ 43 ሺህ 719 የላቦራቶሪ ምርመራ 4 ሺህ 951 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ55 ሰዎች ህይወት ደግሞ በዚሁ ምክንያት አልፏል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በሳምንቱ 4 ሺህ 402 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 83 ሺህ 429 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 37 ሺህ 683 ሆኗል።
እስካሁን በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 277 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 467 ሰዎች መካከል 239 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 343 ሺህ 250 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በየትኛውም ሠዓትና ሁኔታ ለኮሮና ቫይረስ ሊያጋልጡ ከሚችሉ ሁኔታዎች በመጠበቅ ሁሌም የመከላከያ መንገዶችን ያለመሰልቸት ልንተገብራቸው እንደሚገባ የጤና ባለሞያዎች ያሳስባሉ።


@coronainethiopia