Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 841 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 588 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 841 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 588 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 997 የላቦራቶሪ ምርመራ 841 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 85 ሺህ 136 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 588 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 38 ሺህ 904 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 301 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 929 ሰዎች መካከል 230 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 356 ሺህ 630 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@coronainethiopia