Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 865 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 668 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 865 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 668 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
*******************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 24 የላቦራቶሪ ምርመራ 865 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 82 ሺህ 662 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 668 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 102 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 271 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 287 ሰዎች መካከል 243 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 335 ሺህ 856 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@coronainethiopia