Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ 902 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 764 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ******* | Coronavirus in Ethiopia & The rest

በኢትዮጵያ 902 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 764 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 668 የላቦራቶሪ ምርመራ 902 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 81 ሺህ 797 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 764 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 434 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 262 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 099 ሰዎች መካከል 253 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 327 ሺህ 832 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።


@coronaimethiopia