Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ በቁጥጥር ስር ዋለ። የቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋዜጠኛው ግርማይ ገ | Ethio 19

ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋዜጠኛው ግርማይ ገብሩ ዛሬ በመቐለ ከተማ በወታደሮች ቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ አሳወቀ።

የዓይን እማኞች ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩን ወታደሮች ከነበረበት ካፌ ይዘውት ሲሄዱ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ጋዜጠኛው በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋለ እስካሁን የማውቀው ነገር የለም ብሏል ቢቢሲ።

ነገር ግን ጋዜጠኛ ግርማይ እዛው መቐለ ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ መወሰዱን ሪፖርት እንደደረሰው ቢቢሲ ገልጿል።

* ከጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ በተጨማሪ ሌሎች 4 ሰዎች አብረውት ወታደራዊ ልብስ በለበሱ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa