Get Mystery Box with random crypto!

ከ3 ሳምንታት በኃላ እነአቶ ጃዋር መሃመድ በአካል ፍርድ ቤት ቀረቡ : በረሃብ አድማ ላይ እንደሚ | Ethio 19

ከ3 ሳምንታት በኃላ እነአቶ ጃዋር መሃመድ በአካል ፍርድ ቤት ቀረቡ :

በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ዛሬ ረፋድ ላይ ፍርድ ቤት ለነበራቸው ቀጠሮ ሲቀርቡ አካላቸው ደክሞ እና ከስተው መታየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ዛሬ ጠዋት ላይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር።

ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ከጀመሩ 33 ቀናት እንዳለፋቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

በዚህም መሠረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

https://telegra.ph/BBC-NEWS-03-01

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa