Get Mystery Box with random crypto!

ሞጆ ሀዋሳ ! የባቱ - አርሲ ነጌሌ ግንባታ ፦ በእስራኤሉ SBI international h | Construction Proxy

ሞጆ ሀዋሳ !

የባቱ - አርሲ ነጌሌ ግንባታ ፦

በእስራኤሉ SBI international holdings A.G /ኤስ ቢ አይ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግስ ኤ.ጂ ነው/ የሚነናወነው።

የማማከርና ቁጥጥር ስራውን ኩንውሀ ኢንጂነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ከኮሪያ ኤክስፕረስ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ እያከናወኑ ነው።

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆነው ሶስት ቢሊየን ሶስት መቶ አምስት ሚሊየን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ብር እየተሸፈነ የሚገኘው ከአለምባንክ በተገኘ ፋይናንስ ነው፡፡

የአፈር ቆረጣ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ስራዎች፣ የስትራክቸር ፣የውሀ ማፋሰሻ ፣ የአቃፊ ግንብ፣ ትላልቅ የድልድይ ግንባታ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች እና የክሬሸር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

21 ኪ.ሜ የDBM/ ለመጨረሻ የአስፋልን ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተጠናቋል/ ።

አርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የሚዘልቀው የመንገድ ክፍል ፦

ሚገነባው የስራ ተቋራጭ cccc ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ነው።

የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ቤጂንግ ኤክስፕረስ ዌይ ሱፐር ቪዥን ካምፓኒ ሊሚትድ ከውሀን ጄአይኦኬ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ሊሚትድ ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩት ነው ፡፡

መንገዱን ለመገንባት የሚውለውን ወጪ አምስት ቢሊየን አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ብር በቻይናው ኤግዚም ባንክ 85 በመቶ እና 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡

በአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት የአፈር ቆረጣ እና ድልዳሎ ስራ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣የስትራክቸር ስራዎች፣ የሰብ ቤዝ ስራ፣ የውሀ ማፋሰሻ ቱቦዎች ቀበራ ፣ የድልድይ ግንባታ፣ የጠጠር ንጣፍ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡

የ3 ነጥብ 4 ኪ.ሜ ለመጨረሻ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ የDBM ተጀምሯል።

#ERA

@tikvahethiopia