Get Mystery Box with random crypto!

' ለምን ? ብለን ስንጠይቅ ነፃ ገበያ ነው፤ ካዋጣችሁ መግዛት ካልሆነ መተው ትችላላችሁ ይሉናል ' | Construction Proxy

" ለምን ? ብለን ስንጠይቅ ነፃ ገበያ ነው፤ ካዋጣችሁ መግዛት ካልሆነ መተው ትችላላችሁ ይሉናል " - የብረት ነጋዴ

በግንባት እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑ ከተነገረ ወራት አልፈዋል ይህ ጉዳይ አሁን ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ ቀጥሏል።

ዛሬ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይዞት በወጣው መረጃ ላይ እደተመለከትነው ከግንባታ እቃዎች አንዱ በሆነው ፌሮ ብረት ላይ በሳምንት ውስጥ ብቻ የ300 ብር ጭማሪ ታይቷል።

ጋዜጣው ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ በረት ሻጭ የሆኑ አንዲት ነጋዴ ፤ የፌሮ ዋጋ በየዕለቱ፣ በየሰዓቱ ይጨምራል ያሉ ሲሆን ደንበኞች የዋጋ ጭማሪውን ፈርተው መግዛት አቁመዋል ብለዋል።

እኚሁ ብረት ሻጭ እንዳሉት የፌሮ አከፋፋዮች በማንአለብኝነት የውጭ ምንዛሬ ጨምሯል፣ ነፃ ገበያ ነው በማለት አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶች እያቀረቡ ደስ ባላቸው ዋጋ ይሸጣሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ ለጋዜጣው ቃላቸውን የሰጡት የብረት ሻጭ ፤ ከ3 ዓመት በፊት 75 ብር የነበረውና ከ1 ወር በፊት 200 ብር የነበረው ባለ8 ተብሎ የሚጠራ ፌሮ አሁን 500 ብር ገብቷል ብለዋል።

በዋጋ ንረቱ የደንበኞቻቸው ቁጥር መቀነሱንም ገልፀዋል። አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ስራውን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የፌሮ ዋጋ በየጊዜው የሚጨምረው ከፋብሪካው ነው የሚሉት የብረት ሻጯ ፤ " ጠዋት ገዝተን ዕቃውን ለማስጫን ስንሄድ ጨምሯል፤ ብር ጨምሩ እንባላለን " ሲሉ አስረድተዋል።

ምክንያት ሲጠይቁም " ነፃ ገበያ ነው ፤ ካዋጣችሁ መግዛት ካልሆነ መተው ትችላላችሁ የሚል መልስ እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

ያንብቡ https://telegra.ph/EPA-03-30

@tikvahethiopia